Sebhat Amare

Struggle for your freedom

የዜጎችን ስቃይ ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል – ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

Derege Negash

semayawi14ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

መንግስት በሰማያዊ ፖርቲ ላይ የከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በአስቸኳይ ያቁም!!!

ሰማያዊ ፓርቲ በየመን፣ ደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እየተከታተለ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ በእነዚህ ሀገራት ችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል በማውገዝና መንግስትም መፍትሄ እንዲሰጥ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል እንዲያስቆም አዲስ አበባ ለሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ደብዳቤ በመጻፍ ፓርቲያችን የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በተመሳሳይ መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ እርምጃ ለመቃወም የጠራውን ሰልፍም በመደገፍ ሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያው ተቃዋሚ ፓርቲ ነው፡፡

ይሁንና የዜጎችን ስቃይ ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል የፈለገው ሕወሀት ኢህአዴግ ሰማያዊ ፓርቲ በወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው በደል መፍትሄ እንዲሰጥ መወትወቱ፣ የፖለቲካ ልዩነታችን ወደ ጎን አድርገን በሰልፉ ላይ መገኘታችን እንዳላስደሰተው ከሰልፉ ቀን ጀምሮ በፓርቲያችን ላይ የተከፈተው ዘመቻ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ መንግስት ሊቢያ ውስጥ በወገኖቻችን ላይ ለተፈፀመው ጭካኔ ምንም አይነት ትኩረት ባለመስጠቱ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማታቸው ያላሰበውን ሰልፍ ጠርቷል፡፡ በጠራው ሰልፍ ላይም መንግስት…

View original post 484 more words

Single Post Navigation

Leave a comment