Sebhat Amare

Struggle for your freedom

መከራችን መፍትሄ ሳያገኝና ሃዘናችንም ሳይበርድልን ሌላ ከባድ መርዶ ከወደ ሊቢያ ተሰማ

Justice4Ethiopia

ከአብርሃም ተፈሪ (ሚኒሶታ)

ወዳጆች በቅድሚያ በያላችሁበት የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ!
ከዚህ ቀጥሎ የምታነቧት አጭር ጽሁፍ በስራ ገበታየ ላይ ሳለሁ በሃሳብ ወዲህ ወዲያ ስባዝን የሞነጫጨርኳት ሰሞንኛ ማስታወሻ ነች።
Abreham D
ሰሞኑን በኛ ኢትዮጵያኖች ላይ የደረሰብንን የሃዘን ማእበል እንዲህ ነው ብሎ ለመግለጽ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው። በደረሰብን ሃዘን ምክንያት ሁላችንም ልባችን ተሰብሯል ውስጣችንም በቁጭት ተቃጥሎ አሯል። የመን ውስጥ በጦርነት መሃል እየተሰቃዩና እየተገደሉ ስላሉ ወገኖቻችን አዝነን ምን ብናደርግ ይሻላል እያልን እየተወያየን ባለንበት ሁኔታ ሌላ አሰቃቂና ጥላቻን መሰረት ያደረገ ኢ-ሰብዐዊ ድርጊት ከደቡብ አፍሪቃ ተሰማ። በደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ከሃገራቸው ኢትዮጵያ በተለያየ ምክንያት ተሰደው በሰው ሃገር ደከመኝ ሳይሉ ቀን ከሌት ሰርተው በላባቸው የሚኖሩ መሆናቸውን ቀናው የሃገሬው ህዝብ የመሰከረበት የአደባባይ እውነት ነው። ይህንን የኢትዮጵያውያኑን ጥንካሬና ችሎታ ተመልክተው የዙሉ ጎሳ የሆኑት የደቡብ አፍሪቃ ዜጎች ለስራ ሊነሳሱ ሲገባ፤ በተቃራኒው ፍጹም ጥላቻን መሰረት ባደረገ ስሜት ካገራችን ይውጡልን በማለት ሲፎክሩ ተሰምተዋል። ይህም አልበቃ ብሏቸው ኢ-ሰብዐዊ ድርጊታቸውን በወገኖቻችን አንገት ላይ ጎማ በማስገባት በጠራራ ፀሃይ እመንገድ ላይ ቤንዚን አርከፍከፍክፎ በመግደል አሳይተዋል። በዚህም ኢ-ሰብዐዊ በሆነ…

View original post 575 more words

Single Post Navigation

Leave a comment