Sebhat Amare

Struggle for your freedom

‘በረከተ መርገም ‘

”……ኮምፒተር የሚሏት የደብተራ ሳጥን ከመጣች ጀምሮ፣
በወግ መኖር ቀረ አስማት ሆነ ኑሮ፣
ከተፈጥሮ ሸሸ ሰው ከሰው መነነ፣
መኖርና መሞት ክሊክ ማድረግ ሆነ !…”

'በረከተ መርገም 
(በዕውቀቱ ስዩ)
(በቅርቡ በሞት የተለየን ባለቅኔው ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ከሚደነቅባቸው ምርጥ ግጥሞቹ መሃል አንዱ በረከተ መርገምት ይሰኛል፡፡ ወጣቱ ባለቅኔም ታዲያ በዛ አይረሴ የገሞራው ግጥም ስልት ይህ ዘመናችን ላይ ሳቅ እያጫረ የመረገምት በረከቱን ያወርደዋል…)

ነጭና ጥቁር ነው የኔ አመዳም ዓለም፣ 
ቴሌቪዥኔ ግን ባለ ሕብረ ቀለም፣ 
ምንም እንኳ ቲቪው ሳሎኔ ውስጥ ቢኖር፣ 
የቲቪው ኑሮ ግን ሳሎኔ ውስጥ የለም… 
የቆንጆ ሰራዊት የሕንፃ ሰንሰለት፣ 
የማያልቅ አዱኛ የማይነጥፍ ውበት፣ 
ያልፋል በስክሪኔ… 
ይህንን እያየሁ ቀርከሃ ሶፋ ላይ ተኝቻለሁ እኔ፣
እድሜ ለቲቪዬ ለጉምዥት ማሽኔ ! 

የቲቪ ፈብራኪ የልቦና ፍሬ ፍትህ የጎደለው፣
ኢትዮጵያዊው ገብርኤል ቁልቢ ላይ ያለው፣
በነበልባል ሰይፉ በሚንቀለቀለው፣
አንድ ጊዜ ሰንዝሮ ጎንህን ይንቀለው !

ኮምፒተር የሚሏት የደብተራ ሳጥን ከመጣች ጀምሮ፣ 
በወግ መኖር ቀረ አስማት ሆነ ኑሮ፣ 
ከተፈጥሮ ሸሸ ሰው ከሰው መነነ፣
መኖርና መሞት ክሊክ ማድረግ ሆነ ! 

ወንበር ላይ ተጥዶ ወንበር ላይ እንዲያረጅ፣ 
ትውልዴ ላይ አዚም የጣልክበት ፈረንጅ፣ 
የፌስቡክ ፈብራኪ ጎረምሳ ዲታ ሰው፣ 
የግፍ ንብረትህን በልተህ ሳትጨርሰው፣ 
የየካው ሚካኤል አይንህን ያፍሰው !

የሹክሹክታ ዘመን ትላንትና አለፈ፣ 
እንደ ደጋ መስኖ ምላስ ተጠለፈ፣ 
እቤት ተቀምጬ ባለስልጣን ሳማ፣ 
ቤቱ ተቀምጦ አጅሬ እንዲሰማ፣ 
በእጅ የማይዳሰስ የሃሜት ሰንሰለት፣ 
የዘረጋህለት… 
የሞባይል ፈጣሪ የቴሌፎን ጌታ፣ 
በኖርክበት ዘመን ባለህበት ቦታ፣ 
አቡነ አረጋዊ ይጣሉህ በቴስታ !'

በረከተ መርገም (በዕውቀቱ ስዩ)
(በቅርቡ በሞት የተለየን ባለቅኔው ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ከሚደነቅባቸው ምርጥ ግጥሞቹ መሃል አንዱ በረከተ መርገምት ይሰኛል፡፡ ወጣቱ ባለቅኔም ታዲያ በዛ አይረሴ የገሞራው ግጥም ስልት ይህ ዘመናችን ላይ ሳቅ እያጫረ የመረገምት በረከቱን ያወርደዋል…)

ነጭና ጥቁር ነው የኔ አመዳም ዓለም፣
ቴሌቪዥኔ ግን ባለ ሕብረ ቀለም፣
ምንም እንኳ ቲቪው ሳሎኔ ውስጥ ቢኖር፣
የቲቪው ኑሮ ግን ሳሎኔ ውስጥ የለም…
የቆንጆ ሰራዊት የሕንፃ ሰንሰለት፣
የማያልቅ አዱኛ የማይነጥፍ ውበት፣
ያልፋል በስክሪኔ…
ይህንን እያየሁ ቀርከሃ ሶፋ ላይ ተኝቻለሁ እኔ፣
እድሜ ለቲቪዬ ለጉምዥት ማሽኔ !

የቲቪ ፈብራኪ የልቦና ፍሬ ፍትህ የጎደለው፣
ኢትዮጵያዊው ገብርኤል ቁልቢ ላይ ያለው፣
በነበልባል ሰይፉ በሚንቀለቀለው፣
አንድ ጊዜ ሰንዝሮ ጎንህን ይንቀለው !

ኮምፒተር የሚሏት የደብተራ ሳጥን ከመጣች ጀምሮ፣
በወግ መኖር ቀረ አስማት ሆነ ኑሮ፣
ከተፈጥሮ ሸሸ ሰው ከሰው መነነ፣
መኖርና መሞት ክሊክ ማድረግ ሆነ !

ወንበር ላይ ተጥዶ ወንበር ላይ እንዲያረጅ፣
ትውልዴ ላይ አዚም የጣልክበት ፈረንጅ፣
የፌስቡክ ፈብራኪ ጎረምሳ ዲታ ሰው፣
የግፍ ንብረትህን በልተህ ሳትጨርሰው፣
የየካው ሚካኤል አይንህን ያፍሰው !

የሹክሹክታ ዘመን ትላንትና አለፈ፣
እንደ ደጋ መስኖ ምላስ ተጠለፈ፣
እቤት ተቀምጬ ባለስልጣን ሳማ፣
ቤቱ ተቀምጦ አጅሬ እንዲሰማ፣
በእጅ የማይዳሰስ የሃሜት ሰንሰለት፣
የዘረጋህለት…
የሞባይል ፈጣሪ የቴሌፎን ጌታ፣
በኖርክበት ዘመን ባለህበት ቦታ፣
አቡነ አረጋዊ ይጣሉህ በቴስታ !

Single Post Navigation

Leave a comment