Sebhat Amare

Struggle for your freedom

ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የ” ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ” ያወጣው ጽሁፍ

ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የ” ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ” ያወጣው ጽሁፍ

ጋዜጣ (ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) የዛሬ 96 አመት የፃፈው ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ ታሪካዊ ማስረጃ ነው

ኢትዮጵያ በየዘመኗ በሕልውናዋ ላይ የተቃጣባት የመበታተን አደጋን ያለፈችበት መንገድ የጦርነት መንገድ ብቻ አይደለም።ሆኖም ግን ከነበሩን የግጭት ታሪኮች በዘለለ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ እና በሕዝብ ዘንድም የተወደዱ መሪዎች ነበሩን።ከእነኝህ ውስጥ ዳግማዊ ምንሊክ አንዱ ነበሩ። አፄ ምንሊክ ሀገር የማስተዳደር ጥበብን የተማሩት በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሆነው እድገታቸውን በንጉሡ ቤተመንግስት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።ንጉሡ የቀደሙ አባቶቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ አላማቸው እውን እንዲሆን ያደረጉ እድለኛ ንጉስም ናቸው።

አፄ ምንሊክ ኢትዮጵያን አንድ ከማድረግ አልፈው እስከ ኬንያ፣ሱዳን እና ሱማልያ ግዛት ድረስ ዘልቀው ገብተው በቅኝ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ህዝቦችን ነፃ ያወጣሉ የሚል ስጋት የነበረባቸው እና በወቅቱ በእነኚሁ የጎረቤት ሃገራት ላይ የጥቅም ፍላጎት የነበራቸው የአውሮፓ ሃገራት በብርቱ ተፈታትነዋቸው ነበር።በመሆኑም አዲስ የድንበር ውል ከኢትዮጵያ ጋር የመፈራረም ፍላጎት ከእንግሊዝ፣ፈረንሳይ እና ኢጣልያ በኩል ጥያቄ መነጻቱን የወቅቱ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።

ዛሬ ዛሬ በምንሊክ ላይ ታሪካዊ መሰረት የሌላቸው ቀድሞ አፄ ምንሊክ የቅኝ ግዛት ጥማታቸውን በገቱባቸው እና ቂም በያዙ ፀሐፊዎች የተፃፉ ናቸው ብለው ከሚነግሩን አስገራሚ ”የታሪክ” ፅሁፎች ውስጥ ”በምኒሊክ ዘመን እስከ አስር ሚልዮን ኦሮሞዎች አለቁ” የሚል ፅሁፍ በአንዳንድ የማህበራዊ ድህረ ገፆች ተለቀው ሲነበቡ መመልከት አስገራሚ የሰሞኑ ክስተት ነው።በፖለቲካው አለም በቂ ርዕዮተ አለምም ሆነ ፖለቲካዊ ፍልስፍና የጠፋባቸው አንዳንድ ወገኖች ”ትርፋማ” ብለው ያሰቡት የዘር ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን መካከል መዝራት እና ከመቶ አመት በፊት የሆነውን የታሪክ ክስተት የአሁኑን ትውልድ በመውቀስ ትኩረት ለማግኘት ሲታትሩ መመልከት የዘመኑ አስቂኝ ተውኔት ነው።ዳግማዊ ምንሊክ ገና ብዙ የሚጠና ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ወታደራዊ ክህሎት ባለቤት ለመሆናቸው በወቅቱ ከወጡት የዓለማችን ድንቅ ጋዜጦች አንዱ የ ኒውዮርክ ታይምስን እትም መመልከት ይበቃል።

ከእዚህ በታች በሚገኘው የኒውዮርክ ታይምስ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሕዝብ ብዛትን 7,000,000 (ሰባት ሚልዮን) መሆኑን ያስቀምጣል። እዚህ ላይ አንዳንድ እራሳቸውን የታሪክ ምሁራን ነን በሚል ባልተጨበጠ ይልቁንም በምኒሊክ የቅኝ ግዛት ህልማቸው ከተደናቀፈባቸው ቂመኛ ፀሐፊዎች አነበብን የሚሉት እና የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ያማለሉ መስሏቸው ”ምንሊክ 10 ሚልዮን ኦሮሞ ገደሉ” እያሉ ኢትዮጵያ ከነበራት የህዝብ ብዛት (7 ሚልዮን) በላይ ቁጥር ሲጠሩ እፍረት አልተሰማቸውም።

”ማን ያውራ የነበረ” እንዲሉ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ ጋዜጣው አዲስ አበባ በነበረ በልዩ ዘጋቢው አማካይነት ስለንጉሡ እና ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ፅፎ ነበር።ጋዜጣው አፄ ምንሊክ እና አስተዳደራቸውን ከገለፀበት አረፍተ ነገር ውስጥ እነኝህ ይጠቀሳሉ –

– ኢትዮጵያን ወደ ህገመንግስታዊ የንጉሥ አስተዳደር ለመቀየር ሂደት ላይ መሆኗን፣

– የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 7 ሚልዮን መሆኑን፣

– አፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ጦርነት የነበረው የአፄ ዮሐንስ ተተኪ እሳቸው መሆናቸውን ካልተቀበሉት ጋር ብቻ እንደ ነበር፣

– የአውሮፓውያንን ስልጣኔ ወደሀገራቸው ለማምጣት የባርያ ንግድን ከመዋጋታቸውም በላይ ነፃ ትምህርት ዕድል ዜጎች እንዲያገኙ መሰረት መጣላቸውን፣

– ምንሊክ እራሱ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰው መሆናቸውን። ከችሎታዎቻቸው መካከል ዲፕሎማት፣የፋይናንስ ባለሙያ እና ወታደር የሚሉት እንደሚጠቀሱ እና

– እንደ ዲፕሎማት እና ወታደር የጣልያንን ወረራ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ያደረጉበት ጥበብ መሆኑን፣

የሚሉ ይገኙበታል።የጋዜጣውን ሙሉ ፅሁፍ ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።

የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይክፈቱ።

Published: November 7, 1909 Copyright © The New York Times

source – http://72.167.42.24/art/readarticle?artid=146

Advertisements

ያልተዘመረለት ወጣት አርበኛ!

የካቲት 12፤ 1929 ዓ.ም ያልተዘመረለት ወጣት አርበኛ!

ስምኦን አደፍርስ 1905-1929

የካቲት 12 ቀን 1929 .ም አርብ የሚካኤል እለት የፋሽስቱ ሙሶሊኒ የኢትዮጵያ እንደራሴ የነበረውን ሩዶልፎ ግራዚያኒን በቦምብ ለመግደል በገነተ ልዑል ቤተ መንግስት (አሁን አዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ከአብርሃ ደቦጭና ከሞገስ አስገዶም ጋር ከሴራው ጥንስስ ጀምሮ አብሮ የነበረውንና ሰባቱን ቦምቦች አምጥቶ የሰጣቸው፣ ስለቦምብ አጠቃቀም፣ አነቃቀልና አወራወር የሚያውቅ ሰው አፈላልጐ ለተግባር ልምምድ ወደ ዝቋላ ወስዶ እንዲሰለጥኑ ያደረገና ከቦምቡ ጥቃት በኋላም ጓደኞቹን ወደሰላሌ (ፍቼ) ደብረሊባኖስ በራሱ ታክሲ አድርሶ እንዲያመልጡ ያደረጋቸው አብርሃና ሞገስን ባንኮዲሮማ (ኤነሪኮ) አጠገብ በቀጭኑ አስፋልት 50 ሜትር ያህል ርቆ በሚገኘው የእህቱ ቤት (አሁን ጐላን ሄይት ምግብ ቤት) ወስዶ በምስጢር ሴራውን ያደራጀ፣ ነገር ግን የጀግንነትና የአርበኝነት ታሪኩ ከእነሱ ጋር የማይጠቀሰውንና የማይዘከረውን ‹‹አራተኛ ሰው›› ባለታክሲው አርበኛ ስምዖን አደፍርስ አድጐአይቸው የሚባል ሰው መሆኑን ያውቁ ኖሯል?

2011 በታተመው The plot to kill Graziani በተባለው የአያን ካምፕቤል መጽሐፍ ውስጥ ‹‹4ኛው ሰው›› ተብሏል፡፡ ስብሃት ጥሩነህ፣ አብርሃ ደቦጭ፣ ሞገስ አስገዶም እና ስምዖን አደፍርስ ማለት ነው፡፡ ስለየካቲት 12/1929 .ም የዕለተ አርብ ጭፍጨፋ፣ እልቂትና ስለአብርሃ ደቦጭና ስለሞገስ አስገዶም ብዙ የተባለና በሰነድም የሚገኝ በመሆኑ ለተነሳንበት አላማ ስንል እንለፈውና ወደ ያልተዘመረለት ወጣት አርበኛ ስምዖን አደፍርስ አድጐ አይቼው ታሪክ እንዝለቅ፡፡

ስምዖን አደፍርስ ፋሽስቱን ግራዚያኒን ለመግደል በተካሄደው የቦምብ ጥቃት ሴራ ውስጥ የነበረው ሚና በዚያ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በደንብ የሚታወቅ ቢሆንም በጣሊያን ዘገባዎች ላይ ተመስርተው የተፃፉ ሰነዶች ውስጥ ከአብርሃና ከሞገስ በስተቀር ስለ ሶስተኛው የሴራ ቀጥተኛ ተሳታፊ አርበኛ ጉዳይ የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡ ስምዖን አደፍርስ የሐረር ሰው ነው፡፡ በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት በሐብሮ አውራጃ አንጫር ወረዳ ጉባ ላፍቶ ቀበሌ ከአባቱ ከአቶ አደፍርስ አድጐአይቸውና ከእናቱ ከወይዘሮ ወለተ ብርሃን መሸሻ በ1905 .(1912 በፈረንጅ) የተወለደው ስምዖን አደፍርስ ከሰፊ ቤተሰብ የተገኘ ነው፡፡

አራት ወንድሞች ነበሩት፡– – ሱራፌል አደፍርስ፣ አጐናፍር አደፍርስ፣ ደበበ አደፍርስ፣ ከተማ አደፍርስ ስድስት እህቶችም ነበሩት፡– – አሰገደች አደፍርስ ማንያህልሻል አደፍርስየውብሰፈር አደፍርስ ሸዋረገድ አደፍርስ ተሬዛ አደፍርስ (አሁንም በህይወት አሉ ማዘር ተሬዛ ሆነዋል) – እርባን አደፍርስ

በነገራችን ላይ አሁን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ደምረው ሱራፌል ከአርበኛው ስምዖን አደፍርስ ወንድሞች አንዱ የሆኑት የሱራፌል አደፍርስ ልጅ ናቸው፡፡ የአቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ወንድሞችና የስምዖን አደፍርስ የወንድም ልጆች የሆኑት ሰናይት ሱራፌል (ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ የምትኖር)፣ ዘውዱ ሱራፌል (ስዊድን የሚገኝ)፣ አፀደ ሱራፌል (የቤት እመቤት ላፍቶ አካባቢ የምትኖር)፣ ይልማ ሱራፌል (አግሮኖሚስት ኦሮሚያ ግብርና የሚሰራ)፣ ውቢቱ ሱራፌል (አካውንታንት)፣ ሞምባሳ ሱራፌል (በፖለቲካ ሳይንስና የአለም አቀፍ ግንኙነት PSIR ማስተርስ ዲግሪ ያለውና በጥናትና ኮንስልታንሲ ዘርፍ በግሉ እየሰራ የሚገኝ ምሁር፣

/ር አሸብር ሱራፌል (የማህፀንና ጽንስ ስፔሻሊስት አሁን አሰላ ሆስፒታል የሚገኙ) ናቸው፡፡ ለእነዚህ ሁሉ ባለታክሲው አርበኛ ስምዖን አደፍርስ አጐታቸው ነው ማለት ነው፡፡ ዝርዝሩ የቀረበው ለማገናዘቢያነት ይረዳል በሚልና አርበኛው ስምፆን ዘመድ አዝማድ እንደሌለው በማስመሰልና በማስወራት ንብረቱን ወስደው ዛሬም ድረስ ዘመዶቻቸው የሚጠቀሙባቸው የዚያን ግዜ ባንዳዎችና አፋሽ አጐንባሾችን የዘረፋ ድርጊት ለማጋለጥ የሚረዳ በመሆኑ ነው፡፡

ስምዖን አደፍርስ ሐረርጌ ጉባ ላፍቶ በነበረው በሮማን ካቶሊክ ደብር ትምህርት ቤት በፈረንሳይኛ ተናጋሪ መምህራን የተገራና ከነቤተሰቡ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነበር፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በልደታ ማርያም ካቴድራልና በአሊያንስ ፍራንሴ ትምህርት ቤቶች ተምሯል፡፡ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ የተዋጣለት የንግድ ሰው ሆኖ ያን ጊዜ ከስምንት የማይበልጡ ታክሲዎች በነበሩት የትራንስፖርት ዘርፍ ተሰማርቷል፡፡ ከወንድሞቹ አንዱ የሆነው አጐናፍር አደፍርስ ከጅቡቲ በላከለት ሁለት ኦፔል (plymouth የሚልም አለ) መኪናዎች የታክሲ ሥራ ሲሰራ የተከበሩ ደምበኞቹን(ያኔ በታክሲ የሚሄዱ ገንዘብ ያላቸው ብቻ ነበሩ፡፡ ደሃው ታክሲ ብርቁ ነበር፡፡ ከየት አምጥቶስ ይሳፈራል) ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እየጫነ ወደ ባቡር ጣቢያ (ለገሀር) ወደ ግቢ (ቤተመንግስት)ጐቬርኖ ጂነራሌ ወደ የውጭ አገር ለጋሲዮኖችና ወደ ሆቴሎች ያመላልስ ነበር፡፡ ከአብርሃና ከሞገስ አስገዶሞ ጋር የተዋወቁትና የተግባቡት በዚሁ የታክሲ ባለቤትነቱ ምክንያት ነበር፡፡ ሶስቱም በፋሽስት ጣሊያን አገዛዝ የተበሳጩ ግራዚያንን ለመግደል ቆርጠው የተነሱ ወጣቶች ነበሩ፡፡ ስምዖን አደፍርስ ያንጊዜ እድሜው 24 አመት ሲሆን ወንደላጤ (ያላገባ) እና ዘመናዊ ትምህርት የነበረው በመሆኑ የቅኝ ግዛት ሃሳብ (የጣሊያን ቅዥት) የማይዋጥለት የአገሩ ነፃነት የሚያንገበግበው ለዚህም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል የቆረጠ ጀግና ወጣት ነበር፡፡

የካቲት 12 ቀን 1929 .ም አርብ የሚካኤል እለት ከቀኑ 620 ሰዓት ገደማ አብርሃና ሞገስ ግራዚያኒ ላይ በጣሏቸው ቦምቦች ፋሽስት ሳያስበው በደረሰው ድንገተኛ ፍንዳታ ግራዚያኒ ከ200 በላይ በሆኑ የቦምብ ፍንጥርጣሪዎች ተጐድቶ በአፍንጫው ከተደፋበት አንስተው ወደ ኦስፒዳሌ ኢታሊያኖ (አሁን ራስ ደስታ ሆስፒታል) ተወሰደ፡፡ በወቅቱ የአዲስ አበባ ከንቲባ በነበረው ፋሽስት ግዊዶ ኮርቴሲ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በእለቱ ስብሰባ የግራዚያን የጉራ ዲስኩር ለመስማት በግዴታም ሆነ በውዴታ በተጠሩትና ከሁለት ማርያትሬዛ ብር የማትበልጥ ምጽዋት (የጣሊያን ቸርነት) ለመቀበል በመጡ ከሦስት ሺ በላይ በሆኑ የአዲስ አበባ ምንዱባንና በድፍን አገሪቱና አካባቢዎች ላይ በጣሊያን ወታደሮችና በኛዎቹ ባንዳዎች አማካይነት የተፈፀመው ግፍ በታሪክ በማይረሳ ሁኔታና በሰነዶችም ተደግፎ በየዓመቱ እለቱ ሲዘከርና ሲታሰብ የሚኖር በመሆኑ የያኔውን ግፍና ዝርዝር በቁጭትና በሃዘን እናልፈዋለን፡፡ በጥቃቱ ሴራ ወንድሙ ስምዖን አደፍርስ እንዳለበት የሚያውቀው ወንድምየው ሱራፌል አደፍርስ በፋሽስቶች ላለመያዝና ቃሉን ላለመስጠት ሲል ሌሊቱን በእግሩ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በብዙ ድካም ወደተወለደበት ሐረርጌ ሄዶ ቀሪውን እድሜውን እዚያው አሳለፈ፡፡

አብርሃና ሞገስ የቦምብ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ከገነተ ልዑል ቤተመንግሥት በመነን ት/ቤት በር በኩል ወጥተው ስምዖን አደፍርስ መኪናውን ነዳጅ ሞልቶ ሞተሩን አስነስቶ እንዲጠብቃቸው በተነጋገሩት መሰረት ወደዚያው አምርተው በታክሲዋ ገብተው ሄዱ፡፡ በቀጥታ የሄዱት በቀጨኔ በኩል ወጥተው የጐጃምን መንገድ ይዘው በሱልልታ በኩል ወደ ሰላሌ (ፍቼ) ደብረ ሊባኖስ ነበር፡፡ አብርሃ ደቦጭ ከራስ ኃይሉና ከራስ ደስታ ጋር ዝምድና ያላት «ታደለች እስጢፋኖስ» የተባለች ሚስት ነበረችው፡፡ የቦምብ ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት ደብረሊባኖስ ወስዶ እናቷ ጋር እንድትቆይ አድርጐ ነበርና እነሱም ወደዚያው ሄዱ፡፡ እዚያ የደረሱት የካቲት 13/1929 .ም ቅዳሜ እለት ነበር፡፡ እዛው ውለው አደሩ፡፡ በማግስቱ እሁድ የተክለሃይማኖት ቀሳውስት ዝማሬ ላይ በነበሩበት ሰአት አብርሃና ሞገስ ደብረሊባኖስን ለቅቀው ሄዱ፡፡ አላማቸውን በተመለከተ በአካባቢው ከነበሩ አርበኞች ጋር ለመቀላቀል ወደ ኃይለማርያም ማሞ ለመግባት አስበው ነው የሚሉ አሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሄዱት ከራስ አበበ አረጋይ ጋር ለመቀላቀል ወደመርሃ ቤቴ (መገዘዝ) ነው፡፡ ከራስ አበበ ጋርም ተገናኝተዋል ይላሉ፡፡

ወደ «ሶስተኛው ሰውየ» ወደ ስምዖን አደፍረስ እንመለስ፡፡ ባለታክሲው ወጣት አርበኛ ስምዖን አደፍርስ ጓደኞቹን ከተሰናበተና ከሸኘ በኋላ (ደብረሊባኖስ አንድ ሳምንት ቆይቷል) ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ የሚሆነውን ነገር ለማየት ወሰነ፡፡ ጣሊያኖች የሚያደርሱበትን ነገር ሁሉ ለመቀበል ወሰነ፡፡ ስምዖን ከደብረሊባኖስ ለምን ተመለሰ? ለሚለው ጥያቄ የሚቀርቡ አማራጭ ግምታዊ መልሶች ተሰጥተዋል፡፡ ከፊሉ « ለመመለስ የወሰነው በእነሱ ጦስ ፋሽስት አዲስ አበባ ውስጥ የፈፀመውን ግፍ መጠን አልሰማ ይሆናል…» ሲል ሌላው ደግሞ «ያውቃል ግን በሴራው ውስጥ መኖሩን ጣሊያኖች ላያውቁ ይችላሉ የሚል ሃሳብ ኖሮት ይሆናል» ይላል፡፡ ሌሎች በበኩላቸው ‹‹ከቤቱ ጠፍቶ መሰወሩ በሴራው ውስጥ እንደነበረበት ሊያስጠረጥረው ስለሚችል ይህን የፋሽስቶች ጥርጣሬ ለማስወገድ አስቦ ነው›› ይላሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ሳይንስና የአለም አቀፍ ግንኙነት ምሁርና የስምዖን አደፍርስ የወንድም ልጅ የሆነውን ሞምባሳ ሱራፌልን አነጋግሬው ነበር፡፡ የእሱ እምነት ከቤቱ በመጥፋቱ በካራቢኝሪዎች (የፋሽስት ፖሊሶች) ዘንድ ሊያሳድር የሚችለውን ጥርጣሬ ለማስወገድ አስቦ ነው የሚለውን አቋም እንደሚደግፍ ነግሮኛል፡፡ የሆነው ሆኖ ስምዖን አደፍርስ አዲስ አበባ ደርሶ ቤቱ እንደገባ መሰወሩን ከሰራተኛው (አሽከሩ) ባገኙት መረጃ የተረዱትና በቤቱ አካባቢ በቅርብ ሆነው የሚከታተሉት የፋሽስት ሰላዮች ሊይዙት ችለዋል፡፡

ደጃች ውቤ ሰፈር በነበረው የጣሊያን ፖለቲካ ጉዳዮች ጽ/ቤት (UFFicio politico) አጠገብ በነበረው ጊዮርጊስ እስር ቤት (አሁን ት/ቤት ነው) አንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ አስረው ፀጉሩን እየነጩ፣ ጥፍሩን እየነቀሉአናቱን እየቀጠቀጡናመላ ሰውነቱን በብረት እየወቀጡ እንዳይሞት ያህል ብቻ ፍንጃል ውሃ እየሰጡ ታጥቦ የተጨመቀ ጨርቅ እስኪመስል ድረስ አዝለፍለው ሲመረምሩት ከረሙ፡፡ በግራዚያኒ ላይ ቦምብ የጣለው ማን እንደሆነበሴራው የተሳተፉና የደገፉ እነማን እንደነበሩወዘተ እንዲያወጣ አስቃዩት፡፡ ወጣቱ ስምዖን ግን አይበገሬ ሆነባቸው፡፡ አንዲትም ምስጢር ሊያገኙበት አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም የካቲት 29 ቀን 1929 .ም ፋሽስቶች ወደታሰረበት ክፍል ገብተው ገዳይ መርዝ በመርፌ ወግተው ገደሉት፡፡

በዚያን ጊዜ ፋሽስት የገደላቸውን ሰዎች አስከሬን ያቃጥል ነበር፡፡ የወንድሟን መሞት ያወቀችውና አስከሬኑን ከሌሎች 12 አስከሬኖች ጋር በ11 ሰዓት እንደሚያቃጥሉት የተነገራት እህቱ ወ/ሮ ሸዋረገድ አደፍርስ የነበራትን የወርቅ ጌጣጌጦች ለእስር ቤቱ ኃላፊ ዶ/ር ኢያኑዚ ጉቦ ሰጥታ የወንድሟን አስከሬን በድብቅ ለመውሰድ ቻለች፡፡ ግንቦት 1 ቀን 1929 ጥቂት የቤተሰብ አባላት በተገኙበት በአባ ፍራንሷ ማርቆስ መሪነት የካቶሊካውያን መካነ መቃብር በሆነው ጉለሌ በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ ምልክት እንኳ በሌለው ስፍራ በድብቅ ቀበሩት፡፡ የጀግናው አርበኛ የስምዖን አደፍርስ የወንድም ልጅ የሆኑትና በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ብርሃነ እየሱስ ደምረው ሱራፌል ዘገዳመ ላዛሪስት ከ54 ዓመታት ገደማ በኋላ በ1983 በስምዖን አደፍርስ መቃብር ላይ የመታሰቢያ ሃውልት በእምብነ በረድ አቆሙለት፡፡

ጀግናው ወጣት አርበኛ ስምዖን አደፍርስ በግራዚያኒ ላይ ስለተደረገው ሴራ አንድም ምስጢር ያላወጣ ሆኖ ሳለ ጣሊያኖች ለምን ገደሉት? የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ በግራዚያኒ እምነት ስምኦን መሞት ነበረበት፡፡ ምክንያቱም በህይወት ከተረፈ ለአለም የሚደርስ ብዙ የሚያውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡

በተለይ አጥቂዎቹ ኤርትራውያን ከነበሩ (ያኔ ኤርትራ በጣሊያን ስር ነበረች) የአዲስ አበባን (የኢትዮጵያን) ህዝብ መጨፍጨፍ ድርጊቱን ምክንያት አልባ ያደርግበታል። አጥቂዎቹም ሁለት ብቻ መሆናቸው ደግሞ ድፍን የአዲስ አበባ ህዝብ እንዳመፀበት በማስመሰል የወሰደው የእልቂት ርምጃ የፋሽስት አምባገነንነት እነሱን ቀጥሮ ማሠራቱ ጥንቃቄ የጐደለው መሆኑን ለአለም ህዝብና ለሚዲያ የሚያጋልጥና የጣሊያንን መንግስት ስም በአለም መንግስታትና ህዝቦች እንዲሁም በጣሊያን ህዝቦች በራሳቸው ዘንድ ጭምር የሚያጠለሽ ድርጊት ነው። ከዚህም በላይ ግራዚያኒ በዚህ ደደብነቱ የላከውን የጣሊያንን መንግስት አላማ በብልሃት ባለማስፈፀሙ በኢትዮጵያ የሙሶሊኒ እንደራሴ የመሆን ስልጣኑን የሚያስነጥቀውና በመንግስቱና በህዝቡ ፊትም የሚያስነቅፈው ነው። በዚህም ከዚህ በኋላ ለማንኛውም አይነት ስልጣን ቦታ የማያገኝ ስለሚያደርገው ከሴራው ጋር የነበረውንና ይህን ሁሉ ጉድ በግልጽ የሚያውቀውን ስምዖን አደፍርስን መርዝ ወግተው እንዲገድሉት አደረገ፡፡ ጀግናው አርበኛ ሰማዕት በጣሊያኖች መርዝ ይሙት እንጂ ባለፈውም ሆነ በአሁኑና በመጪው ዘመን ትውልድና የኢትዮጵያ ታሪክ ልብ ውስጥ ዘለአለም ስሙ በእግዚአብሔር ጣት በወርቅ ፊደላት ተቀርፆ ይኖራል፡፡

ስለ የካቲት 12/1929 .ም ፀረ ግራዚያኒ ሴራ ዝግጅትና አፈፃፀም ምስጢራት ሁሉ በተሟላ ሁኔታ የሚያውቀው ብቸኛ ሰው በመሞቱ እሱ ብቻ ሊመልሳቸው የሚችሉ በርካታ ጥያቄዎች ለታሪክ ምሁራን ጥናትና የቃል መረጃነት ግምት ተዳርገው ቀርተዋል፡፡

የጀግናው ኢትዮጵያዊ አርበኛ ሰማዕት የስምዖን አደፍርስ ታሪክ በታሪክ ሰነዶች ሳይሰፍር ለብዙ ዓመታት ቆይቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ «በባንዳዎች ተጽዕኖና ከድል በኋላ አርበኛ ነን» ብለው አፋሽ አጎንባሽ በሆኑ ሸፍጠኞች ደባ መሆኑ በተቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በእርግጥ የአርበኛው ሰምዖን አደፍርስ የአርበኝነት ታሪክ በአንዳንድ የህትመት ውጤቶች ላይ መታየት ጀምሯል፡፡ በዋነኛነት፡አዲስ ዘመን ጋዜጣ ሐምሌ 18 ቀን 1977 .«ምን ሰርተው ታወቁበተባለ አምድ ስር «ሰምዖን አደፍርስ /1905-1929/ አርበኛው ታክሲ ነጂ» በሚል ርዕስ ታሪኩን አስፍሯል፡፡

አዲስ ዘመን ጋዜጣ የካቲት 12 ቀን 1979 .«የየካቲት እልቂትና የታሪክ ምስክሮች» በሚል ርዕስ የሪቻርድ ፓንክረስትን ምስክርነት ጠቅሶ ሰምዖን አደፍርስ ፣ አብርሃና ሞገስ ቦምቡን ከጣሉ በኋላ በመነን ት/ቤት በር በኩል መኪናውን ይዞ ይጠብቃቸው ነበርና ተሳፍረው ከኃይለማርያም ማሞ ጋር ለመቀላቀል ወደ ፍቼ አድርሶ መመለሱን ጽፏል፡፡

አዲስ ዘመን የካቲት 13 ቀን 1993 .«64ኛው የሰማዕታት ቀን ታስቦ ዋለ» በሚል ርዕስ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ሊቀመንበር አቶ አሰፋ ባዩ ስለ አብርሃ ሞገስና ስለ ስምዖን አደፍርስ ቆራጥነት፣ አርበኝነትና ጀግንነት መናገራቸውን አስፍሯል፡፡

•Addis Tribune February 27/2004 (በፈረንጅ) who was the third man? በሚል ርዕስ ፓንክረስት ስለ ስምዖን አደፍርስ ሚና የሰጡትን ምስክርነት አስፍሯል፡፡

በሪሳ ኤብሳ በ1977 ስምዖን አደፍርስ (1905-1929) በሚል ርዕስ ታሪኩን አስፍሯል፡፡

በኢትዮጵያ ሬዲዮ መጋቢት 25 ቀን 1978 .ም እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መጋቢት ወር 1978 .ም ታላቅ እህቱ የወ/ሮ አሰገደች አደፍርስን ቃለመጠይቅና ዘገባ ተላልፏል፡፡

ከነዚህ ውጭ Ian Campbell IES Bulletin No 35-40/2004 እትም ላይ ስለስምዖን አደፍርስ ጽሑፍ አቅርቧል፡፡

2011 Ian Campbell; The plot to kill Graziani የተባ መጽሐፍ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ በኩል አሳትሟል፡፡ ለገበያም ቀርቧል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የስምኦን አደፍርስ ስም ከ50 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡

በእርግጥ የስምኦን አደፍርስ ታሪክ በኢትዮጵያ አርበኞች ታሪክ ተመዝግቧል፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬም ሆነ ወደፊት የዚህን ታላቅ የኢትዮጵያ ባለውለታ ጀግና አርበኛ ወጣት ሰማዕት ታሪክ በሚመለከት በአርበኞች ማህበርም ሆነ በመንግስት አማካይነት የሚከተሉት ተግባራት ቢደረጉስ? የምንላቸው ጉዳዮች አሉን፡፡

መጀመሪያ ነገር የካቲት 12 ቀን በየዓመቱ ሲከበር የሚጠቀሰው የአብርሃ ደቦጭና የሞገስ አስገዶም ገድል ብቻ በመሆኑ የስምኦን አደፍርስም ታሪክ ከእነሱ ጋር አብሮ መዘከርና የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝና ለወጣቱ አገር ተረካቢ ትውልድ በትምህርታዊነቱና በአርአያነቱ የሚጠቀስ እንዲሆን ቢደረግ፤ ለዚህ ጀግና አርበኛና ሰማዕት ለስሙ መታሰቢያ ት/ቤት፣ መንገድ፣ ሆስፒታልወዘተ መንግስት ቢሰይምለትስ፤ በአርበኛው ሰማዕት መካነ መቃብር ላይ ለአርበኝነቱ የሚመጥን የመታሰቢያ ሃውልት ቢቆምለት፤ አብርሃና ሞገስ በግራዚያኒ ላይ አደጋ ካደረሱ በኋላ ወደሰላሌ የሄዱባት፣ ለቦምብ ውርወራ ስልጠና ዝቋላ የተመላለሱባት ከሴራው ጋር ለተያያዙ ሌሎች ጠቃሚ ተልዕኮዎች የተጠቀሙባት ያቺ የስምኦን አደፍርስ ንብረት የሆነች ታሪካዊት መኪና በአሁኑ ወቅት በግለሰቦች እጅ የምትገኝ ስለሆነ መንግስት ተከታትሎ በታሪክ ኢግዚብትነት በሙዚየም እንድትቀመጥ ቢደረግ የሚል የግል ሃሳብ አለኝ።

ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ሰማዕታት ልጆቿን እያከበረች ለዘላለም ትኑር!

source – http://www.ethpress.gov.et/addiszemen/index.php/addiszemen/editorial/8169-12-1929

ጀግኖቻችን ጌጦቻችን ናቸው

1231118_701891029832797_49942077_nዐርብ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ቀትር ላይ በግራዚያኒ ላይ ቦምብ የወረወሩት አብርሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ናቸው፡፡ የዚህ አደጋ ቀያሽ ሆኖ የሚቆጠረው አብርሃ ደቦጭ እና ጓደኛው ሞገስ አስገዶም የኢጣሊያ ወረራ ሲጀመር አዲስ አበባ በሚገኘው የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነበሩ፡፡ አብርሐ ደቦጭ ቀደም ብሎ የኢጣሊያ ቋንቋ ተምሮ ስለ ነበር ከወረራው በኋላ አዲስ አበባ ባለው የፋሺስት ፖለቲካ ቢሮ ተቀጥሮ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ አብርሃ ደቦጭ ይህ ስራው የፋሺስቶችን የግፍ አገዛዝና የዘር መድልዎ አሠራር በቅርብ ለማወቅ ስላስቻለው ጉዳዩን ከሞገስ አስገዶም እና ስብሐት ከተባለ በጀርመን ቆንስላ ከሚሰራ ጓደኛው ጋር ይወያይበት ነበር፡፡
ይህ ሁኔታም በፋሺስቶች ላይ እንዴት አደጋ መጣል እንዳለባቸው እንዲያውጠነጥኑ አድርጓቸዋል፡፡ አብርሐ ደቦጭ ወደፊት ላቀደው ጸረ ፋሺስት ጥቃት እንዲረዳው በባዶ እግሩ ከአዲስ አበባ 10 እና 15 ኪሎሜትሮች እየወጣ በጫካ ውስጥ ፈንጂ ለመወርወር የሚያስፈልገውን ልምምድ ያከናውን ነበር፡፡
አብርሐ ደቦጭ የቤት ዕቃዎቹን ሸጦ ባለቤቱን ደግሞ ወደ ደብረ ሊባኖስ ወስዶ በማስቀመጡ በፋሺስቶች ላይ አደጋ የሚጥልበትን ቀን አስቀድሞ የሚያውቀው ይመስላል፡፡ አብርሐ ደቦጭ በዚህ ዝግጅት ላይ እያለ ግራዚያኒ በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ድሆችን በመጥራት ምጽዋት ለመስጠት መወሰኑ ተሰማ፡፡ የካቲት 12 ቀን አብርሐ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ከእንቅልፋቸው የነቁት ማልደው ሲሆን፣ የፋሺስት ኢጣሊያን ባንዲራ የሚኖሩበት ቤት ወለል ላይ በጦር ሰፍተውና የእጅ ቦምቦቻቸውን አዘጋጅተው ወደ ገነተ ልዑል ቤተመንግሥት አመሩ፡፡ በሥፍራው እንደደረሱም ወደ ዒላማቸው በድንጋይ ውርወራ ርቀት ያህል ቀረብ ካሉ በኋላ አመቺ ጊዜ ይጠባበቁ ጀመር፡፡ ስድስት ሰዓት ሆኖ ማርሻል ግራዚያኒ ንግግር ማድረግ ሲጀምር አከታትለው የእጅ ቦምቦችን ወረወሩበት፡፡ ፍንዳታው ያስከተለው ረብሻ ከመረጋጋቱና ፋሺስቶችም የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት፣ አብርሀ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በቤተ መንግሥቱ የጓሮ በር ሹልክ ብለው ለመውጣት ችለዋል፡፡ ሞገስ አስገዶምና አብርሃ ደቦጭም ቦንቡን ወርውረው ግራዚያንን አቆሰሉት። ከዚያም ከ30ሺ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪ ተገደለ ተጨፈጨፈ።
ፋሺስት ኢጣሊያ በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የተጣለውን አደጋ ተዋናዮች አብርሐ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም መሆናቸውን ተረድቶ ስለነበር ‹‹አማጽያኑን›› ለሚይዝ ማንኛውም ሰው የ10 ሺህ ሊሬ ሽልማት እንደሚሰጥ አውጆ ነበር፡፡ አብርሃምና ሞገስ ግን መላውን የአዲስ አበባ ነዋሪ ያብረከረከው ጅምላ ጭፍጨፋ ሳይነካቸው ከመናገሻ ከተማው በሰላም ወጥተው ደብረ ሊባኖስ ለመድረስ ችለው ነበር፡፡ በዚያ ከደረሱ በኋላ በራስ አበበ አረጋይ ከሚመሩት የሸዋ አርበኞች ጋር መቀላቀላቸው ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ኤርትራውያኑ ወጣቶች ከኢጣሊያኖች ጋር ይሠሩ ስለነበረ የሸዋ አርበኞቹ እምነት ስላልጣሉባቸው ወደ ሱዳን ለመሄድ ፈቃድ ጠይቀው እንደተሰናበቱ ይታወቃል፡፡
ሁለቱ ወጣቶቹ በጎጃም በኩል አድርገው ወደ ሱዳን ለመግባት ጥቂት ሲቀራቸው በድንበር አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ፡፡ የየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ጅምላ ጭፍጨፋ ከደረሰ ከአራት ዓመታት በኋላ ለብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን ስደት፣ ስቃይና እልቂት ምክንያት የነበረው የፋሺስት ኢጣሊያ የግፍ አገዛዝ የሚያከትምበት ጊዜ መጣ፡፡ ኢትዮጵያውያን በገዛ አገራቸው እንደ አውሬ የሚታደኑብት የጨለማ ጊዜ አልፎ ግፈኞቹ ፋሺስቶች በተሸናፊነት ለኢትዮጵያ አርበኞችና ለእንግሊዝ ሠራዊት እጃቸውን የሚሠጡበት ጊዜ ሲደርስ እውነተኛው የነጻነት ደወል በመላው ኢትዮጵያ አስተጋባ፡፡ የወደቀውና የተዋረደው የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ከአምስት ዓመታት በኋላ እንደገና በኩራት ከፍ ብሎ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ሲውለበለብ፤ የፋሺስት ባንዲራ፣ የፋሺስት የቀበሮ እና የአሞራ አርማና ሐውልት እየተቀደደ እና እየተነቀለ የትም ተጣለ፡፡

ምንጮች –

http://www.harep.org/Africa/biography%20-%20Abraha%20Deboch%20and%20Mogos%20Asgedom.pdf

http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=11918:%E1%8B%9D%E1%8A%AD%E1%88%A8-%E1%88%B0%E1%88%9B%E1%8B%95%E1%89%B3%E1%89%B5-%E1%8B%98%E1%8B%A8%E1%8A%AB%E1%89%B2%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%88%A5%E1%88%AB-%E1%88%81%E1%88%88%E1%89%B5&Itemid=209

‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

• ”ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

• ”12 ፓርቲዎችን በዕጣ አልፋችኋል ለማለት ለ80 ፓርቲ ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?” ወይንሸት ሞላ

አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡images

ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል

ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ ሲገባ፣ በሌላ በኩል ህዝብ የሚፈልገው ሰማያዊን የመሰለ ፓርቲ ዕጣ ውስጥ ገብቶ አላለፈም እየተባለ ነው፡፡ በአንድ በኩል ህዝብ የተማረረባቸው ያለ ቅድመ ሁኔታ ህዝብን እንደሚያንቀሳቅስ የሚታወቀው ሰማያዊ ደግሞ ህዝብ ስፈለገው አሊያም በጥንካሬው ሳይሆን በሎተሪ ወድቀሃል ተብሏል›› ሂደቱ የተሳሳተ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ  ”ሠማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ እጩዎች ተሰረዙብኝ አለ” በሚል ርዕስ አዲስ አድማስ እንደዘገበው —

”የፓርላማ ምርጫ እጩዎች ኢህአዴግ 501፣ መድረክ 303፣ ኢዴፓ 280
የሌላ ፓርቲ አባላትን በእጩነት አስመዝግቧል” – ምርጫ ቦርድ

ሠማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ክልሎች ለፓርላማ ካስመዘገባቸው 400 እጩዎች ግማሽ ያህሉ በምርጫ ቦርድ እንደተሠረዙበት ሲገልፅ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫው  የሌላ ፓርቲ አባላትን ማስመዝገቡ ህገወጥ  እንደሆነ ገለፀ፡፡
ለፓርላማ ኢህአዴግ 501 እጩዎችን፣ መድረክ 303 እጩዎችን፣  ኢዴፓ 280 እጩዎችን አቅርበዋል፡፡ ለፓርላማ ካስመዘገብናቸው እጩዎች ከሁለት መቶ በላይ ተሰርዘውብናል ያሉት  የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንሻንጉል፣ በምዕራብ ጐጃም፣ በከምባታ፣ በሲዳሞ፣ በጋሞጐፋ፣ በአዲስ አበባ፣ በደቡብ ጐንደር እና በሌሎች አካባቢዎች አሣማኝ ባልሆነ ምክንያት እጩዎቻችን ከምርጫ ውጪ ተደርገውብናል ብለዋል፡፡
ፓርቲው የምርጫ አስፈፃሚዎችን እንዳነጋገረ ኢ/ር ይልቃል ጠቁመው፤ እጩዎቻችንን የተሰረዙት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጣ ትዕዛዝ እንደሆነ ተነግሮናል ብለዋል፡፡ “የሌሎች ፓርቲዎችን አባላት አስመዝግባችኋል፤ ትብብር የሚባል ህገ ወጥ አደረጃጀት መስርታችኋል የሚሉ ምክንያቶችንም ሰምተናል ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ በአዲስ አበባ የተሠረዙብን እጩዎች ግን ግልፅ ምክንያት አልተሰጣቸውም ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከፓርላማ ምርጫ የተሠረዙት እጩዎች የተሠረዙበት ምክንያት እንዲነገራቸው ጠይቀዋል፤ ምርጫ አስፈፃሚዎች የሰጡን ምላሽ፤ “እናንተን ለመመዝገብ እኛ ችግር የለብንም፤ ግን እንዳንመዘግብ ከበላይ አካል ታዘናል፤ በደብዳቤ ምላሽ ልንሠጣችሁ አንችልም” የሚል ነው ብለዋል – ኢ/ር ይልቃል፡፡
በጉዳዩ ላይ ከምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ለማግኘት እንደሞከሩና፤ የቦርዱ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነጋ ዱሪሳ በማመልከቻ ካልጠየቃችሁ መልስ አልሰጥም እንዳሏቸው ኢ/ር ይልቃል ተናግረዋል፡፡
የእጩዎች ስረዛን በተመለከተ ከአዲስ አድማስ ለቀረበላቸው ጥያቄ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በሰጡት ምላሽ፤ “የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት” የተሰኘ ፓርቲ አባላቱን በሰማያዊ ፓርቲ ስም በእጩነት እንዳስመዘገበ በመግለፁ ነው ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን ማጣራት የጀመረው ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በማያውቀው ሁኔታ ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ትብብር መስርቻለሁ በሚል መንፈስ፤ የበርካታ ፓርቲዎች አባላት በሰማያዊ ፓርቲ ስም እጩ ሆነው ቀርበዋል ያሉት አቶ ወንድሙ፤ የደቡብ ኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር ራሳቸው በሰማያዊ ፓርቲ ስም አዲስ አበባ ላይ ተመዝግበው መገኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ አንድ  ፓርቲ የሌላን ፓርቲ አባል በእጩነት ማስመዝገብ አይችልም፤ ህገወጥ ነው ያሉት የምርጫ ቦርድ ም/ኃላፊው፤ ስለዚህ የአንድ ፓርቲ አባል በሌላ ፓርቲ ስም እጩ መሆን ስለሌለበት አጣርታችሁ መዝግቡ የሚል መመሪያ አስተላልፈናል ብለዋል፡፡
ቦርዱ የሰጠው መመሪያ እጩ እንዳትመዘግቡ የሚል ሳይሆን እያጣራችሁ መዝግቡ የሚል  ነው ያሉት አቶ ወንድሙ፤ በዚህ አሰራር ደስተኛ ያልሆነ ማንኛውም ፓርቲ፤ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ቅሬታውን ከምርጫ ጣቢያ እስከ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው ማመልከት እንዲሁም ለፍ/ቤት አቤቱታ አቅርቦ  ውሳኔ ማግኘት ይችላል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢህአዴግ፤ ለፓርላማ 501፣ ለክልል ምክርቤቶች ከ1300 በላይ እጩዎችን አቅርቧል፡፡ አራት ፓርቲዎች የተጣመሩበት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፤ ለፓርላማ 303፣ ለክልል ም/ቤቶች ከ800 በላይ እጩዎችን ያቀረበ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) 168 እጩዎችን ለፓርላማ 475 እጩዎችን ለክልል ምክር ቤት አስመዝግቧል፡፡
በኢትዮጵያ ማህበረ ዲሞክራሲ – ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲም 83 ለፓርላማ 273 ለክልል ማቅረቡን ጠቁሟል፡፡ ሌላው የመድረክ አባል አረና ፓርቲ 33 እጩዎች ለፓርላማ 70 ለክልል አቅርቧል፡፡ ኢዴፓ በበኩሉ 280 እጩዎችን ለፓርላማ 200 እጩዎችን ለክልል አስመዝግቧል፡፡ ”

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በዕጩነት እንዳይቀርቡ ተደረገ

• ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ዕጩዎች ‹‹አትወዳደሩም›› ተባሉ
• ‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
• ‹‹12 ፓርቲዎችን በዕጣ አልፋችኋል ለማለት ለ80 ፓርቲ ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?›› ወይንሸት ሞላ
• ‹‹ከምርጫ ቦርድ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡ መዝግቡ የተባልነውን መዝግበናል›› የምርጫ አስፈጻሚዎች

Eng.Yilkal Getnet

አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡

ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል

ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ ሲገባ፣ በሌላ በኩል ህዝብ የሚፈልገው ሰማያዊን የመሰለ ፓርቲ ዕጣ ውስጥ ገብቶ አላለፈም እየተባለ ነው፡፡ በአንድ በኩል ህዝብ የተማረረባቸው ያለ ቅድመ ሁኔታ ህዝብን እንደሚያንቀሳቅስ የሚታወቀው ሰማያዊ ደግሞ ህዝብ ስፈለገው አሊያም በጥንካሬው ሳይሆን በሎተሪ ወድቀሃል ተብሏል›› ሂደቱ የተሳሳተ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ሌሎች የሰማያዊ ዕጩዎች ‹‹አትወዳደሩም›› ተባሉ

• ‹‹12 ፓርቲዎችን በዕጣ አልፋችኋል ለማለት ለ80 ፓርቲ ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?›› ወይንሸት ሞላ

• ‹‹ከምርጫ ቦርድ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡ መዝግቡ የተባልነውን መዝግበናል›› የምርጫ አስፈጻሚዎች

በአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሰማያዊ ፓርቲን ወክላ ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት ቀርባ የነበረችው ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ሌሎችም አዲስ አበባ ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡ ዕጩዎች ‹‹ዕጣው ስላልደረሳችሁ አትወዳደሩም›› መባላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ከወይንሸት ሞላ በተጨማሪ ብሌን መስፍንና አማኑኤል አዱኛ የተባሉ የሰማያዊ ዕጩዎች ‹‹ዕጣው አልደረሳችሁም›› ተብለው ከዕጩነት ውጭ ሆነዋል፡፡

ወይንሸት ሞላ ‹‹ዕጣው አልደረሰሽም›› በተባለችበት የምርጫ ጣቢያ የክልል ፓርቲዎችን የወከሉ ዕጩዎች አልፈዋል የተባሉ ሲሆን ወይንሸት ‹‹የክልል ፓርቲዎች ድምጽ ያሰባሰቡት በየክልሉ እንጅ አዲስ አበባ አይደለም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ሐገራዊ ፓርቲ ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ መራጭ የሌላቸው ፓርቲው በዕጣ አለፉ ተብሎ ሐገራዊ ፓርቲ የሆነው ሰማያዊ ወድቋል መባሉ ያለንበትን ስርዓት በድንብ የሚያጋልጥ ነው፡፡›› ስትል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡

በወረዳ 7 17 ፓርቲዎችን የወከሉ ዕጩዎች የቀረቡ ሲሆን 12 ያለፉ ሲሆን ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች አምስት ፓርቲዎች ‹‹ዕጣው አልደረሳችሁም›› ተብለዋል፡፡ በወቅቱ ወይንሸት ሞላ ለምርጫ አስፈጻሚዎች ‹‹12 ፓርቲዎችን በዕጣ አልፋችኋል ለማለት ለ80 ፓርቲ ፈቃድ መስጠት ለምን አስፈለገ?›› የሚል ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን የምርጫ አስፈጻሚዎችም ‹‹ይህ ከምርጫ ቦርድ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡ መዝግቡ የተባልነውን ነው የመዘገብነው›› የሚል መልስ እንደተሰጣት ገልጻለች፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ ዕጩዎች የታገዱበት ሲሆን በዛሬው ዕለት ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነትም ‹‹ዕጣው አልደረሰህም›› ተብለው በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸው ይታወቃል፡፡

Minilik Salsawi

በእንጦጦ ማርያም ሙዚየም የወርቅ መስቀሎች ጠፍተዋል መባሉ ተቃውሞ አስነሳ

Freedom4Ethiopian

በእንጦጦ ማርያም ሙዚየም የወርቅ መስቀሎች ጠፍተዋል መባሉ ተቃውሞ አስነሳ

‹‹የተባለው ሁሉ ሐሰትና ምንም የጠፋ ነገር የለም›› የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ
-‹‹ከመንግሥትና ከሀገረ ስብከቱ አጣሪ ኮሚቴ ተሰይሞ እየተመረመረ ነው›› የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት

ለርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ከተለያዩ ምዕመናን በስለትና በስጦታ የተሰጡና እስከ አራት ኪሎ ግራም ሊመዝኑ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የወርቅ ሐብል፣ በቅርስነት ከተቀመጡበት ሙዚየም ውስጥ መጥፋታቸውን የደብሩ ካህናትና የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ ካህናት፣ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች የደብሩን አስተዳዳሪና ሌሎች ኃላፊዎች ተባብረው ወርቆቹን ማጥፋታቸውን፣ በቤተ ክርስቲያኗ ሠራተኞች ላይ በደልና ብልሹ አሠራር እንዲደርስ ማድረጋቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት፣ ለሀገረ ስብከቱ ቅርሳ ቅርስ ክፍል፣ ለአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በፊርማ የተረጋገጠ ተቃውሟቸውን አስገብተዋል፡፡

የደብሩ ካህናት፣ የተለያዩ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ በቤተ ክርስቲያኗ የቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየም ውስጥ የአፄ ምኒልክ የወርቅ ጫማ፣ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የተለያዩ አልባሳት፣ አልጋና ብዛት ያላቸው በተለያዩ ምክንያቶች ለቤተ…

View original post 566 more words

Addis Abeba University to host debate among political parties የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሊያከራክር ነው

Derege Negash

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የፖለቲካ ፓርቲዎች በርዕዮት ዓለማቸው ዙሪያ ክርክር የሚያካሂዱበትን መድረክ እንደሚያዘጋጅ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ።
የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት ከዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር የካቲት 21 የሚያካሂደው ክርክር ህጋዊ እውቅና ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አማራጫቸውንና የርዕዮት ዓለም ፍልስፍናቸውን በነፃነት የሚያንሸራሽሩበት ይሆናል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት ኃላፊ ዶክተር አብዲሳ ዘርዓይ ለኢዜአ እንደተናገሩት በአገሪቱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የርዕዮት ዓለም ፍልስፍና ከሦስት ማዕቀፎች አያልፍም።
በዚህም መሰረት የልማታዊ ዴሞክራሲ፣ የሶሻል ዴሞክራሲና የሊበራል ዴሞክራሲ የርዕዮት ዓለምን እናራምዳለን የሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወክለው ክርክራቸውን ያደርጋሉ።
ዶክተር አብዲሳ እንዳሉት ሦስቱን የርዕዮት ዓለም ፍልስፍናዎች ወክለው በክርክሩ ለሚቀርቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ለእያንዳንዳቸው የ30 ደቂቃ የመከራከሪያ ጊዜ ይሰጣቸዋል።
በአገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና አግኝተው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በክርክር መድረኩ ላይ ይታደማሉ።
በሦስቱ የርዕዮት ዓለም ፍልስፍናዎች ዙሪያ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሃሳብ ወክለው የሚያደርጉት አዎንታዊ የመድረክ ላይ ክርክርም የአገሪቱን የዴሞክራሲ ስርዓት በማጎልበት ረገድ የላቀ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው በክርክር መድረኩ ለሚሳተፉ የፖለቲካ  ፓርቲዎች…

View original post 29 more words

አርበኞች ግንቦት7 – የሰላም በሮች ሲዘጉ የሁለገብ ትግል ስልት በሮች ይከፈታሉ!

January 29, 2015

የሰላም በሮች ሲዘጉ የሁለገብ ትግል ስልት በሮች ይከፈታሉ!

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ አማካይነት እየደረሰበት ያለውን በደል ለሕዝብ ለማሰማት ጥር 17 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ጂንካና ሸዋ ሮቢት የተቃውሞ ሰልፎችን ጠርቶ ነበር። በተለይ በአዲስ አበባው ሰልፍ ላይ የተገኙ ወገኖቻችን ለህወሓት ፍጹም ታማኝ በሆነው የፓሊስ ክፍል ያለርህራሄ መደብደባቸው እና የተቃውሞ ሰልፉም በጉልበት መበተኑ ነፃነትና ፍትህ ናፋቂውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሳዘነ ብቻ ሳይሆነ ያስቆጨ ጉዳይ ነው። በመላው ዓለም በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የተለመደውን ድንጋይ ውርወራ እንኳን ሳይከጅሉ፤ የፓሊሶችን ሰብዓዊ ርህራሄ ለማግኘት “ፓሊስ የኛ ነው” እያሉ እየዘመሩ በፓሊስ ተደበደቡ። ሴቶችና አዛውንት ብቻ ሳይሆን ተላላፊ መንገደኞች እንኳን ከፓሊስ ዱላ አላመለጡም። ከሁሉም በላይ የሚዘገንነው ደግሞ የ 7 ወራት ነብሰ ጡር ሴትም በፓሊስ መመታትዋና ሆዷ መረገጡ ነው። ይህ እኩይ ተግባር የሚፈጥረው ቁጭት በህወሓት ላይ ብቻ አያበቃም። ትዝብቱ ለፓሊስም ተርፏል። ይህ የጭካኔ ተግባር ለፍትህና ለነፃነት በሚደረገው ትግል የሕዝብ አጋር ይሆናል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የፓሊስ ሠራዊትን የሚያዋርድ ነው። ደካማ እናቶችን፣ አረጋዊያንን፣ ባዶ እጃቸውን ተቃውሞ እያሰሙ ያሉትን ወጣቶችንና ነፍሰጡሮችን በጭካኔ መደብደብ ለራሱና ለሥራው ክብር ለሚሰማው ፓሊስ ውርደት ነው፤ የሞት ሞት ነው። የኢትዮጵያ የፓሊስ ሠራዊት አባላት ተግባራቸው ያሳፍራቸዋል፣ ይቆጫቸዋል፤ ቁጭታቸውንም ይህን ትዕዛዝ በሰጡ አለቆቻቸው ላይ በግልም ሆነ በተደራጀ መንገድ በሚወስዱት እርምጃ እናያለን ብሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ ያደርጋል።

የጥር 17 ቀን 2007ቱ ሽብር በአንድ ወቅት የተፈጠረ፤ በአንድነት ፓርቲ ላይ ብቻ ያነጣጠረ፣ የተናጠል ክስተት ሳይሆን ህወሓት ደግሞ ደጋግሞ ሲፈጽመው የነበረ ነው። ከዚህ በፊት በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ፈጽሞታል። የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላንን በተቃወሙ የተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎች በተለይም በአምቦ ላይ የብዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሽብር ነዝቷል። በቅርቡ ደግሞ በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ተመሳሳይ አረመናዊ ድርጊት ፈጽሟል።

አርበኞች ግንቦት 7: ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የህወሓት ታጣቂዎች በወገኖቻችን ላይ ያደረሱትን ድብደባ፣ ህገወጥ እስር፣ እና የተቃውሞ ሰልፍ ክልከላን አጥብቆ ይቃወማል። አርበኞች ግንቦት 7፣ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው ህመም ህመሙ፣ ቁስላቸው ቁስሉ ነው።

ባለፉት ሃያ ሶስት ተከታታይ ዓመታት፣ በአምቦ፣ በጅማና በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞችና ገጠሮች፣ በባህዳር፣በጎንደርና በበርካታ የአማራ ከተሞችና ገጠሮች፣ በጋምቤላ፣ በሶማሊ፣ በአፋር፤ በአጠቃላይ በመላው ኢትዮጵያ በየአስፋልቱ፣ በየሜዳውና በየጥሻው በህወሓትና ተላላኪዎቻቸው የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያምናል። አርበኞች ግንቦት 7 ከሌሎች መሰል ድርጅቶች ጋር በመተባበር የህወሓትን እድሜ በማሳጠር የእናቶቻችን እምባ ሊያብስ ዝግጁ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ኢትዮጵዊያን እንደከብት እየተደበደቡ ወደ ማጎሪያ የሚያጋዙበት እና በጠገቡ ሰላዮችና ፓሊሶች እየታነቁ የሚታረዱበት ጊዜ ማብቃት አለበት ይላል።

የቱን ያህል ቢለመንም ሆነ ቢወገዝ ህወሓት ለነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒን ምርጫ ዝግጁ ሊሆን ቀርቶ በምርጫ የሚወዳደሩት ፓርቲዎች እነማን እንደሆኑና እነማን በእጩ ተወዳደሪነት መቅረብ እንዳለባቸው ሳይቀር የሚወስን ዓይን አውጣ አጭበርባሪ ድርጅት ነው። ይህንን ከዚህ በፊት አይተነዋል፤ አሁንም በአንድነትና በመኢአድ ላይ እየተደገመ ነው። ህወሓት፣ በየአምስቱ ዓመታቱ በሚያደርጋቸው የሴራ ምርጫዎች በሚቀጥሉት አርባና ከዚያም በላይ ለሆኑ ዓመታት በሥልጣን ላይ የሚቆይበትን ስልት ቀይሶ የሚንቀሳቀስ፤ ኢትዮጵያን ለብዙ ዓመታት ለመግዛት ማድረግ የሚችለውን ክፋት ሁሉ ከማድረግ የማይመለስ አገር በቀል ቅኝ ገዥ ነው። ህወሓት የዘረጋው ሥርዓት ህገ-አልባነት፣ ፀረ-ሕዝብነት እና አምባገንነት ለማጋለጥ በሚል ርህራሄን በማያውቁ የሥርዓቱ አገልጋዮች ፊት ባዶ እጅ መጋፈጥ የሚፈጥረው የሞራል የበላይነትና የመንፈስ ጀግንነት ባያጠራጥርም የሚያስከፍለው ዋጋ ከሚገኘው ውጤት ጋር ማመዛዘን ግን እጅግ ተገቢ የሆነ የማይታለፍ ሥራ ነው ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከህወሓት የሴራ ምርጫ ፋይዳ ያለው ውጤት ይገኛል ብሎ አይጠብቅም። ከምርጫው የሚፈልገው ውጤት አንድ ነገር ብቻ ነው፤ እሱም የመንግሥት ለውጥ ነው። ምርጫው በምርጫነቱ ወደ መንግሥት ለውጥ አያደርስም፤ ወደ መንግሥት ለውጥ ወደሚያመራ ሕዝባዊ አብዮት ሊያሸጋግር ግን ይችላል። ይህም ቢሆን የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ በተለይም የሠራዊቱን ዓይነትና አደራጀጀት እግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ መታቀድ ይኖርበታል።

አርበኞች ግንቦት 7 የራሱን ጥናት አድርጎ ለኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ እና ህወሓትን ለመሰለ ጠላት የሚመጥን የትግል ስልት ሁሉንም የትግል ስልቶች እንደሁኔታው ያዳቀለ – ሁለገብ – መሆን ይኖርበታል ብሎ ወስኖ ለተግባራዊነቱ እየተንቀሳቀሰ ነው። ሁለገብ የትግል ስልት ሕዝባዊ ተቃውሞን፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነትንና ሕዝባዊ አመጽን እንደወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ ማፈራረቅና ማደባለቅን ይፈልጋል። ሰላማዊ ትግል በተለይም ሕዝባዊ እምቢተኝነት ሲባል ደግሞ ህወሓት ያወጣቸው አፋኝ ህጎች እያከበሩ የሚደረግ አለመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይረዳል። ሁለገብ ትግል በተቻለ መጠን የወገን ኃይል ራሱን ፈጽሞ መከላከል በማይችልበት ሁኔታ እንዳይገኝ ለማድረግ ይጥራል። በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት ሁለገብ የትግል ስልት ሰፊ ተቀባይነት የሚያገኝበት ወቅት ደርሷል። ከዚህ በፊት “የሰላም በሮች ሲዘጉ የአመጽ በሮች ይከፈታሉ” ተብሎ በአንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ታጋይ የተነገረው “የሰላም በሮች ሲዘጉ የሁለገብ ትግል ስልት በሮች ይከፈታሉ” በሚል እንዲሻሻልና በዚህ ወለል ብሎ በተከፈተው በር ሁላችንም እንድንገባ አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል። በሁለገብ የትግል ስልት በሰላማዊ መንገድ የሚደረጉ የትግል ዓይነቶች አሉ፤ በሌላም መንገድ የሚደረጉ አሉ። ስለሆነም በሁለገብ ትግል እያንዳንዳችን እንደየዝንባሌዓችንና እንደየችሎታዎቻችን አስተዋጽኦ ልናበረክት የምንችልበት ሰፊ እድል ይከፍትልናል።

ስለሆነም፣ በዚህ አጋጣሚ አርበኞች ግንቦት 7፣ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለጦር ሠራዊትና ፓሊስ አባላት ወገናዊ ጥሪ ያደርጋል።

በህወሓት ዘረኛ አገዛዝ በሚደርስብን ውርደት፣ እንግልት፣ ስደት፣ ሥራ አጥነትና ድህነት የተማረራችሁ እና እኩልነቷ የተረጋገጠ፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት የምትመኙ ሁሉ የሁለገብ የትግል ስልትን አዋጪነት እንድታጤኑ የዚሁ ስልት አካል ሆናችሁ እንድትታገሉ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።

የኢትዮጵያ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት በግል ከሚደርስባችሁ ግፍ በተጨማሪ የገዛ ራሳችሁን ወገኖች መግደላችሁ፣ ማቁሰላችሁ፣ ማድማታችሁና መደብደባችሁ የህሊና እረፍት ሊነሳችሁ ይገባል። ህሊናችሁ እረፍት የሚያገኘው የሥርዓቱ እድሜ ሲያጥር መሆኑን በመገንዘብ ለገዛ ራሳችሁ ክብር፣ ለወገናችሁና ለአገራችሁ ስትሉ ፋሽስቱን ወያኔ ከድታችሁ ከአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል ጋር ተቀላቀሉ።

እነዚህን ጥሪዎች ተግባራዊ ካደረግን ወገኖቻችን መሠረታዊ መብቶቻቸውን በመጠየቃቸው በመወደስ ፋንታ በፓሊስ ዱላ ሲደበደቡ የማናይበት ዘመን ይመጣል። ይህ ካልሆነ ግን “ውሀና መብራት አጣን” ብሎ አቤቱታ ማሰማት እንኳን በጥይት የሚያስገድልበት ቀን ይመጣል። ያ ከመሆኑ በፊት እንወስን፤ ራሳችንና አገራችን ከህወሓት ዘረኛ አገዛዝ ነፃ እናውጣ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

http://ecadforum.com/Amharic/archives/14277/?utm_source=feedburner&utm_medium=twitter&utm_campaign=Feed%3A%20ecadforum%2FHvBQ%20%28ECADF%20Ethiopian%20News%29

የዓለም ባንክ የሞራል ኪሳራ በኢትዮጵያ

– ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም –

– ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ –

– Jan 28th, 2015 –

ኢትዮጵያውያን/ት ለዓለም ባንክ የጭካኔ ቢሮክራሲያዊ የቀልድ ማካሄጃ የመድረክ ትወና ዒላማነት ተዳርገዋል፡፡

dollar-billበምዕራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ እየተባለ በሚጠራው ክልል የዓለም ባንክ ቢሮክራቶች ዜጎችን ከሰፈሩበት ቦታ ያለፈቃዳቸውወደ ሌላ ቦታ በማዛወር፣የአካባቢው ዜጎች በቋሚነት ባህላቸውን አዳብረው ከሚኖሩበት ቦታቸው በግዳጅ በማፈናቀል እናየተለሳለሰና እና በጎ መስሎ በእሬት የተለወሰ የዘርማጽዳት እኩይ ምግባር በማካሄድ “የማታለል ጨዋታ” በመጫወት ላይመሆኑን አንድ ያለም ባንክ የራሱ የምርመራ ዘገባ ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል፡፡ በጋምቤላ ክልል በቋሚነት የሚኖሩ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የአኙዋክ ብሄረሰብ ተወላጆችን ጥንት ቀደምቶቻቸው ይኖሩበት ከነበረው ቀያቸውየሚያፈናቅል ፖሊሲንበመንደፍ ዓለም ባንክ ህገወጥ በሆነ መልኩ ምንም ዓይነት ውኃ በማይገኝበት እና ሌሎችም መሰረታዊ አገልግሎቶችባልተሟሉበትአካባቢ በግዳጅ ተፈናቅለው እዲሰፍሩ በማድረግ በአሁኑ ጊዜ የተፈናቃዮች ህይወት በቋፍ ላይ ወይም ደግሞምንም ዓይነት ተስፋ ሊሰጥ በማይችልአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ተንጠልጥሎ ይገኛል፡፡

ለበርካታ ዓመታት የዓለም ባንክ ቢሮክራቶች እና በኢትዮጵያ ያሉ ተመሳሳዮቻቸው በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት)አምባገነናዊ ወሮ በላ ቡድንበመካሄድ ላይ ባለው “የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ ፕሮጀክት” እየተባለ በሚጠራው እና“በመንደር ምስረታ ፕሮግራም” መካከል አለ እየተባለየሚነገረውን መሰረታዊ ግንኙነት ሙልጭ አድርጎ በመካድ ህዝቡንበሚጎዳ ድርጊት ላይ ሙዝዝ ብለው ይገኛሉ፡፡ (“የመንደር ምስረታ ፕሮግራም”የሚለውን ቃል የአኟክ ብሄረሰብ ኗሪዎችጥንታዊ ቀደምቶቻቸው ይኖሩበት ከነበረው ኋላቀር የአኗኗር ዘይቤ ተላቅቀው “በዘመናዊ መልክ በስልጣኔ”መኖር መቻልነው ከሚለው ቃል ጋር መሳ ለመሳ ያደርጉታል፡፡) የዓለም ባንክ ዓይን ባወጣ መልኩ በጋምቤላ ክልል ከመሰረታዊአገልግሎት ጥበቃፕሮጀክት (መአጥፕ) ጋር በተያያዘ መልኩ የሚቀርቡበትን ትችቶች ባለመቀበል ምንም ዓይነት የሰብአዊመብት ረገጣዎች ለመፈጸማቸው ሊያመላክቱየሚችሉ ማስረጃዎች የሉም በማለት በተደጋጋሚ በማስተባበል ላይ ይገኛል፡፡

የህዝቡ ፍላጎት ተገዥ ለመሆን ተባባሪ ያለመሆን፣ ህዝቡን ከፍላጎቱ ውጭ በኃይል በማስገደድ እንዲሰፍር ማድረግ እና ሆንብሎ የሀሰት ወሬዎችንማሰራጨት የዓለም ባንክ፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት መምሪያእና በኢትዮጵያ የልማት እርዳታ ቡድን (27የሁለትዮሽ እና የብዙሀን መንግስታትን አካትቶ የያዘ ስብስብ) እየተባለየሚጠራው በኢትዮጵያ የተጠያቂነት ጉዳይ በሚነሳበት ጊዜ የሰብአዊ መብት ረገጣወንጀል መፈጸማቸው እንዳይታወቅለመከላከያነት የሚጠቀሙባቸው ስልቶች ናቸው፡፡ የእንግሊዝ ፓርላማ ዓለም አቀፍ የልማት ኮሚቴ ሊቀመንበርየሆኑት ጌታማልኮም ብሩስ እ.ኤ.አ ማርች 2013 እንዲህ በማለት በድፍረት ተናግረዋል፣ “ስለመንደር ምስረታው የሚነገሩ አሉባልታዎችሁሉ መሰረተቢስናቸው፣ እናም የእንግሊዝ ፕሮግራም ጥሩ ውጤት እየሰጠ ነው፡፡“

የአቤ ሊንኮልን አባባል በመዋስ “የዓለም ባንክ እና የድህነት ወትዋች አቃጣሪዎች “የልማት እርዳታ ቡድን” እየተባለየሚጠራው የበርካታ ሀገሮች ስብስብሁሉንም ኢትዮጵያውያንን/ትን አንድ ጊዜ ሊያታልል ይችላል፣ እንደዚሁም ደግሞጥቂት ኢትዮጵያውያንን/ትን ሁልጊዜ ሊያታልል ይችላል፣ ሆኖም ግንሁሉንም ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያውያት ሁልጊዜሊያታልል አይችልም፡፡“ እነዚህ የጉሮሮ ላይ አልቀቶች (ተባይ) በሚጫወቱት የማታለል ጨዋታ ምክንያትኢትዮጵያውያን/ትተታለዋል! ተጭበርብረዋል! እንዲሳሳቱ እና ግራ እንዲጋቡ ተደርገዋል፡፡ የማልኮምን አባባል በመዋስ “ኢትዮጵያውያን/ትጭካኔበተሞላበት ሁኔታ የጉልበታሙ የዓለም ባንክ መጫወቻ አሻንጉሊት ተደርገዋል፡፡“

ስለሆነም ከዓለም ባንክ ነጻ “የተጠያቂነት የምርመራ ቡድን” (ኢንስፔክሺን ፓኔል) (ምቡ) ጋር መነጋገር አስፈላጊ ነው፡፡በእርግጥ ምቡ ንጹህ በሚመስል፣በተበጣጠሰ እና ቢሮክራሲያዊ በሆነ የቋንቋ አገላለጽ ይናገራል፡፡ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ እናስሜታዊነት የተሞላባቸው እንቆቅልሽ የሆኑ አስደንጋጭ የሆነየሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ቋንቋ በፍጹም አይጠቀሙም፡፡የሰዎች ሰብአዊ መብቶች በይፋ እየተደፈጠጡ እያዩ ድርጊቱን የሞራል ኪሳራ ብለውአይናገሩም፡፡ ሸክስፒር በሮሚዮ እናጁሌት እንዲህ በማለት ጽፈዋል፣ “እነዚህን እንቆቅልሾች ግልጽ እስከምናደርግ ድረስ ለጊዜው የሞራል ስብዕና ኪሳራንአፍእንዲሸበብ ያደርጋሉ…” ይህንን አስደንጋጭ ሁኔታ እንዲዳፈን አላደርግም ምክንያቱም የዓለም ባንክ የእራሱ የምርመራ ቡድንሁሉንም እንቆቅልሽ የሆኑነገሮች ሁሉ ግልጽ አድርጎልኛልና!

እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 2012 ሁለት ደርዘን እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ በምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልል የሚገኙኢትዮያውያን/ት የመጠለያ ላይ ተረጅዎችቀደምቶቻቸው ይኖሩበት ከነበረው መሬታቸው በግዳጅ እንዲፈናቀሉ ተደርገውየመሬት ይዞታቸው ለመሬት ነጣቂዎች የተሰጠ መሆኑን በመግለጽ ይህእኩይ ድርጊት እንዲጣራላቸው ዓለም ባንክንጠይቀው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 24/2012 አንድ ስሙ ባልተገለጸ የአኟክ ተረጅ በተጻፈ ደብዳቤ በዓለምባንክ የገንዘብድጋፍ እየተደረገለት የሚተገበረው የኢትዮጵያ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ ፕሮጀክት (መአጥፕ) እና በቀጥታየኢትዮጵያን “መንግስት”የመንደር ምስረታ ፕሮግራም የሚረዳውን የዓለም ባንክን ክፉኛ ወንጅሏል፡፡ በተለይም፣

1ኛ) በመአጥፕ ፕሮግራም የአኟክ ቋሚ ኗሪዎች ይኖሩበት ከነበረው ለም ከሆነው መሬታቸው በግዳጅ እንዲፈናቀሉ ተደርገውመሬታቸው ኢንቨስተርእየተባሉ ለሚጠሩ መሬት ተቀራማቾች በርካሽ ዋጋ በኪራይ ይሰጣል፣

2ኛ) የአኟክ ማኅበረሰብ አባላት ለእርሻ ምቹ ባልሆኑ እና ለምነታቸው በተሟጠጠ ጠፍ መሬቶች ላይ እንዲሰፍሩ ሆኖ አዲስመንደሮች እንዲመሰርቱይገደዳሉ፣

3ኛ) የተሻሻሉ የማህበራዊ አገልግሎቶችን ለህዝቡ በማቅረብ የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ እናሻሽላለን በሚል የውሸትማደናገሪያ ብዙሀኑ ህዝብ ከኖረበትቀየው በግዳጅ እንዲፈናቀል ይደረጋል፡፡ ሆኖም ግን ሰፋሪዎቹ አንድ ጊዜ ከሰፈራ ቦታውከደረሱ በኋላ ለም የሆነ መሬት ብቻ አይደለም የማያገኙት ሆኖምግን ትምህርት ቤቶች፣ ክሊኒኮች፣ የውኃ ጉድጓዶች ወይምደግሞ ሌሎችንም መሰረታዊ አገልግሎቶች ጭምር አያገኙም እንጅ፣

4ኛ) አኟኮች የመኸር ሰብሎቻቸው ለመሰብሰብ በደረሱበት ጊዜ ሰብሎቻቸውን ሳይሰበስቡ እንዳለ ትተው በግዳጅእንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ ሰፋሪዎችበመንግስት በግዳጅ እንዲንቀሳቀሱ በሚደረግበት ጊዜ ከመንግስት ምንም ዓይነትየምግብ እርዳታ አይሰጣቸውም፣ እና አብዛኞቹ ሰፋሪዎች በረሀብ አለንጋእንዲገረፉ ይደረጋል፡፡ በመንደር ምስረታፕሮግራሙ ምክንያት ጥቂት ለአደጋ ተጋላጭ ህዝቦች እና ህጻናት በሚከሰተው ረሀብ ምክንያት ህይወታቸውንያጣሉ፡፡

5ኛ) ደመወዛቸው በህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት (መአጥፕ) እየተከፈላቸው በወረዳ የሚሰሩ የመንግስትሰራተኞች ይህንን ፕሮግራም በተግባርላይ እንዲያውሉት ይገደዳሉ፣

6ኛ) የሰፈራ ፕሮግራሙን የሚቃወሙ አርሶ አደሮች እና ፕሮግራሙን በስራ ላይ ለማዋል ተቃዋሚ የሆኑ የመንግስትሰራተኞች፣ የሰፈራ ጠያቂዎች እናየእነርሱን ዘመዶች ጨምሮ በቁጥጥር ስር የመዋል፣ የድብደባ፣ የማሰቃየት እና የግድያ ሰለባዒላማ የመሆን ዕድል ይጠብቃቸዋል፣

7ኛ) የሰፈራ ጠያቂዎች እነዚህ ሁሉ ጉዳቶች የሚመጡት ከዓለም ባንክ የትግበራ ፖሊሲዎች እና ከአሰራር ሂደቶች አናሳነትእና መስተጋብራዊ ቅንጅትጉድለት ነው የሚል እምነት አላቸው፡፡

እ.ኤ.አ በ2012 “ሞትን ቁጭ ብሎ መጠበቅ፡ በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል ህዝቦችን ማፈናቀል እና የመንደር ምስረታ“ በሚልርዕስ ሂዩማን ራይትስ ዎችየተባለው ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ባለ 115 ገጽ ዘገባ አቅርቦ ነበር፡፡ ያዘገባ በአኟክ ህዝቦች ቀርቦ የነበረውን ውንጀላ አግባብ በሆነመልኩ የደገፈ እና የልማት ድጋፍ ቡድኑን ስህተቶች እናጉድለቶች ነቅሶ በማውጣት በኢትዮጵያ በመንደር ምስረታ ፕሮግራም ሰበብ ታላቅ ውርደት እናውደቀትን ያስከተለ መሆኑንዘገባው ይፋ አድረጓል፡፡ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ እንዲህ በማለት የማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥቷል፡

የኢትዮጵያ መንግስት በመንደር ምስረታ ፕሮግራሙ አማካይነት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩትን በምዕራብ ጋምቤላ ለዘመናትከቀደምቶቻቸው ጀምሮ ሰፍረውከቆዩባቸው ቀዬዎች በግዳጅ በማፈናቀል ወደ አልለመዱት እና አዲስ ወደሆኑ አካባቢዎችእንዲሰፍሩ አድርጓል፡፡ እንደዚህ ያሉት ህዝቦችን ከአንድ ቦታወደ ሌላ ቦታ የማፈናቀሉ ፕረግራም ምንም ዓይነት ጥናት እናምክክር ያልተደረገበት እና ለግዳጅ መፈናቀሉ ሰለባ ለሆኑት ወገኖችም ምንም ዓይነት ካሳሳይሰጥ የተካሄደ ፕሮግራምነበር፡፡

መንግስት መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን እና የመሰረተ ልማት አውታሮችን ለማሟላት ቃል የገባ ቢሆንም አዲሶቹ የሰፈራመንደሮች የምግብ እጥረትያለባቸው፣ የግብርና ድጋፍ ጨርሶ የሌለበት፣ የጤና እና የትምህርት አገልግሎቶች ፈጽሞየሌሉባቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡ የሰፈራ ፕሮግራሙንየሚቃወሙ ካሉ እነዚህን ሰዎች በማስፈራራት፣ አደጋ በማድረስ፣ እናከህግ አግባብ ውጭ የዘፈቀደ እስራትን በማካሄድ በግዳጅ በመከናወን ላይ የሚገኝየሰፈራ ፕሮግራም ነው፡፡ ባለፈው ዓመትየመንግስት የደህንነት ኃይሎች ቢያንስ 20 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን በመፈጸም የሰፈራ ፕሮግራሙንአስቸጋሪነትየበለጠ ውስብስብ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ፍርኃት እና ማስፈራራት በጥቃቱ ሰለባ ህዝቦች ላይ በገፍ ተንሰራፍተውይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ እየፈጸመ ባለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ወንጀሎች ላይ ያለው እውነታ፣

የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን የአኟክ ህዝቦች ያቀረቡትን ቅሬታ በመቀበል አጣሪ ኮሚቴ እንዲሄድ እና እንዲያጣራበማድረግ እ.ኤ.አ ኖቬምበር 21/2014የምርመራ ውጤት የሆነውን ዘገባ በማዘጋጀት ዘገባው ለውስጥ ፍጆታ ብቻ እንዲውልበማድረግ ለዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት፣ ለዋና አስፈጻሚ ዳሬክተሮች፣ለመምሪያ ኃላፊዎች እና ለሌሎች እንዲደርስአሰራጭቷል፡፡ ይህ ውሱን ስርጭት ያለው የምርመራ ዘገባ የዓለም ባንክ ስራ አስኪያጆችን የስራ ግድየለሽነትደረጃንለማሳየት እና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ስራ አስኪያጆች እና በሌሎች አገሮች ያሉት አለቆች ድርጊት በዓለም ህዝብ ዘንድእንዲታወቅ በማሰብሚስጥራዊ በሆነ መልኩ በድረ ገጽ ላይ እንዲለቀቅ ብቻ ነበር የተደረገው፡፡ ግን የሚስጥሩ ዘገባባልታወቀ መንገድ ለሕዝብ አንድከፋፈል ተደርግዋል ።

የምርመራ ቡድኑ “ኢትዮጵያ፡ ክፍል 3 የመሰረታዊ አገልግሎቶችን ማስፋፋት (P128891)” በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን እጅግበጣም አስደንጋጭ እና ለህሊናየሚዘገንን ዘገባ አቅርቧል፡፡ (የጥናቱን ግኝት የበለጠ አጽንኦ ለመስጠት በማሰብ የፊደሎቹፎንቶች ደማቅ ቀለም እንዲሆኑ እና ልዩ የሆኑ ግኝቶችንለማመላከት በተራ ቁጥርነት የሚያገለግሎ ቁጥሮችም በሮማውያንእንዲሆኑ አድርጊያለሁ፡፡)

[ለአንባቢዎቸ ማስታወሻ፡ በምርመራ ቡድኑ በቀረበው ዘገባ መሰረት አንባቢዎቸ የጥናቱን ግኝቶች በጥንቃቄ እናበጥሞናእንድታነቡ እጠይቃለሁ፡፡ አብዛኞቹ አንባቢዎች በቢሮክራሲያዊ የማደናገሪያ ቃላት እና ሀረጎች የቋንቋአጠቃቀም ምክንያትሊያደናግሩ እና በቀላሉም ግንዛቤ ለመውሰድ አስቸጋሪ ሊሆኑ እንደሚቸሉ ይታመናል፡፡ባለስልጣኖች የዘገባውን መግለጫበሚሰጡበት ወቅት ወዲያውኑ ከስር የእንግሊዝኛውን (በቀላል አማርኛ)ትርጉም አዘጋጅቸዋለሁ፡፡]
[I]…የቡድኑ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው የፕሮጅክቱ አስተዳደር በአራት ክልሎች ሊተገበር የተዘጋጀውን የክፍል 3የመሰረታዊ አገልግሎቶች የጉዳትትንተና/risk analysis ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት ፈጽሞ አላከናወነም፣ ወይም ደግሞበየጊዜው ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮች ማቀለያ የሚሆኑ የመፍትሄእርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችሉ በቂ የሆኑ ዝግጅቶችአልተደረጉም፡፡ የምርመራ ቡድኑ እንዳረጋገጠው የአስተዳደሩ አቀራረብ ደረጃውን የጠበቀወይም ደግሞ የጉዳቱ ሰለባሊሆኑ ለሚችሉት የማህበረሰብ ክፍሎች አስቀድሞ በመከለካያነት ሊያገለግል የሚችል አጠቃላይ የሆነ የጉዳት ትንተናየድርጊትማዕቀፍ መመሪያ (ጉትድማመ) በተሟላ መልኩ እና በበቂ ሁኔታ ተዘጋጅቶ አልቀረበም፡፡ የምርራ ቡድኑ እነዚህየተዘለሉ እና የተረሱ ነገሮችን በፕሮጀክትሰነዱ 2.20 ከተቀመጠው ጋር ሊሄዱ እንዳልቻሉ እና ይልቁንም ከዚህ ጋር በተጻረረመልኩ እንደሆኑ በግልጽ አሳይቷል፡፡

[II] … በህዝብ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ክፍል 3 ፕሮጀክት ማጽደቅ ወቅት እና ከላይ እንደተጠቀሰው ፕሮጀከቱንለመተግበር በሚደረጉ እንቅስቃሴዎችጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉት ጉዳቶች በቂ በሆነ መልኩ ጥናት ያልተካሄደባቸው ወይምደግሞ በአግባቡ ያልተያዙ እንዲሁም በክፍል 3 የፕሮጀክት ትግበራወቅት ሊከሰቱ የሚችሉን ጉዳቶች እንዴት ማስወገድእንደሚቻል ያልተየ እንደነበር የምርመራ ቡድኑ ግለጽ አድርጓል፡፡

[III] በማስፈጸሚያ የፕሮጀክት ሰነዱ ቁጥር 4.10 ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የፕሮጀክት አስተዳደሩ ይህ የህዝብመሰረታዊ አገልግሎት ክፍል 3 ሰነድሲዘጋጅ ከዚህ ጋር እኩል ተመጣጣኝ የሆነ ወይም የበለጠ ጥቅም ለአካባቢውህብረተሰብ ሊሰጥ ይገባ ነበር፡፡ የጥናት ቡድኑ ከአኟክ ህዝብ ጋር ቀጥተኛግንኙነት ያላቸውን እንደ የኑሮ ሁኔታ፣ ደህንነት፣መሬት እና የተፈጥሮ ሀብቶች የማግኘት መብትን የፕሮጀክቱ ክፍል 3 የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶችሰነድ ሲዘጋጅእንዲካተቱ አላደረግም፡፡ በሌላ በኩል እነዚህ መሰረታዊ ነገሮች እንዳሉ በሙሉ ከግንዛቤ ውስጥ ሳይወሰዱ የተዘለሉ ስለሆነከፕሮጀክት ሰነዱቁጥር 4.10 ጋር በተጻረረ መልኩ ተግባራዊ ሳይደረጉ ቀርተዋል፡፡

[IV] … ከባንኩ ፖሊሲዎች አንጻር የህብረተሰቡን የልማት ፕሮግራም እና የህዝቡን መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከማረጋገጥአኳያ በትግበራ አካሄዱ መካከልበፕሮጀክት ሰነድ ማጽደቅ እና በትግበራ ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶች እና ችግሮችበተለይም እንደ ጋምቤላ ባለ ክልል ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነውቤተሰብ የመንግስት የልማት የሰፈራ ፕሮግራም እናየመሰረታዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ በሆነበት ማህበረሰብ ውስጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መታየትነበረበት፡፡ በምርመራ ቡድኑየጥናት ግኝት መሰረት በጋምቤላ መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን በግብርናው ዘርፍ እና በሌሎች የኑሮ ሁኔታዎች በጥራትእናበበቂ ሁኔታ ለማግኘት እንዲቻል የፕሮጀክቱ አስተዳደር በየጊዜው የሚከሰቱ ችግሮችን እና ችግሮቹን ለማስወገድ በስራ ላይየሚውሉ የአካሄድስልቶችን ከግንዛቤ በማስገባት በሰነዱ ላይ እንዲካተቱ አላደረግም፡፡

[V]…የክፍል 3 የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ትግበራ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 3 የጋራ የምክክር ፕሮግራሞች እናየትግበራ ድጋፍ ተልዕኮዎችተካሂደዋል፣ ሆኖም ግን ከላይ በቀረቡት ጉዳዮች ላይ የቀረቡ ዘገባዎች ምንም ነገር ትንፍሽ ሳይሉእንዲታለፍ አድርገዋል፡፡ የምርመራ ቡድኑ የክትትል እናየቁጥጥር ስርዓቱ በፖሊሲው ላይ ከተጠቀሰው በተጻረረ መልኩተግባራዊ ሆኗል፡፡

[VI]… የምርመራ ቡድኑ ይፋ እንዳደረገው በሰነዱ ላይ በተራ ቁጥር 10.02 በተጠቀሰው መሰረት የፕሮጀክት አስተዳደሩከተቀመጡት መስፈርቶች አንጻርበህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ክፍል 3 ዝግጅት እና ማጽደቅ ጊዜ እየታዩ ተግባራዊእንዲሆኑ አላደረግም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የምርመራ ቡድኑለመጠቆም እንደሞከረው ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያየተመደበው ገንዘብ በወረዳ ደረጃ ቁጥጥር እና ክትትል እየተደረገበት በስራ ላይ ይውላል የሚለውየባንኩ እምነት ቀጣይነትባለው ሁኔታ ሊካሄድ እንደማይችል የጥናት ቡድኑ በግልጽ አሳውቋል፡፡

[VII]…የልማት ፕሮጀክት ቢሮው የውጤት አመልካቾች በመጀመሪያው የዕቅድ እና በተከታታይም የገንዘብ ብክነት አደጋአናሳ መሆኑን ቢያመላክቱምበቀጣዮቹ ጊዚያት ሊፈጸም ስለሚችልበት ሁኔታ ግን የተዘጋጀ ነገር እንደሌለ የጥናት ቡድኑጠቁሟል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እነዚህ ከገንዘብ አጠቃቀም ጋርየተያያዙ ጉዳዮችን ለመቆጣጠር እና ለመከታተል እየተደረገያለው ጥረት በፕሮጀክት ሰነዱ ላይ የተገለጸው ከባንኩ ፖሊሲ OP/BP 10.00 ጋር ተጻራሪበሆነ መልኩ የተቀመጠ ነው፡፡

የምርመራ ቡድኑ ዘገባ በቀላል የእንግሊዝኛ (አማርኛ ) ቋንቋ ሲተረጎም፣

የቢሮክራቶች ቋንቋ ቢሮክራሲያዊ አገላለጽ ወይም ደግሞ ባለስልጣናዊነት መንፈስ የሰፈረበት ሆኖ ይገኛል፡፡ በቀላሉ ግንዛቤሊወሰድባቸው በማይችሉ፣አደናጋሪ በሆኑ፣ በአዳዲስ የአባባል ቃላት እና ሀረጎች የተሞሉ፣ መንታ ምላሶችየሚግተለተሉባቸው፣ አዳዲስ ስያሜዎች የሚጎርፉባቸው፣ ቀጥተኛ ባልሆኑአገላለጾች የተሸሞነሞኑ፣ እንደሰም እና ወርቅዓይነት አቀራረብ የታጀለባቸው እና በቀላሉ ግልጽ ሊሆኑ በማይችሉ አደናጋሪ አህጽሮተ ቃላት እና ሀረጎችየተሞሉ ናቸው፡፡ቢሮክራሲያዊነት ስለግልጽነት እጦት ጉዳይ ነው፣ ግልጽ ያለመሆን ወይም ደግሞ ቀጥተኛ ሆኖ ያለመቅረብ ጉዳይ ነው፡፡ቢሮክራሲያዊዘገባዎች ሁልጊዜ ግልጽነት የጎደላቸው፣ የተጣመሙ እና የተንሻፈፉ እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ ለማንበብወይም ደግሞ አንብቦ ግንዛቤ ለመውሰድ በጣምአስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን እንዲያደናግሩ እና ቀልብ እንዲያሳጡ ሆነውየተዘጋጁ የሸፍጥ ሰነዶች ናቸው፡፡

ጉዳዩን ግልጽ ለማድረግ በቢሮክራሲው የተካነ እና ቅስናውን የወሰደ የቢሮክራት ጠቢብ በፍጹም አካፋን አካፋ ብሎ በቀጥታአይጠራም፡፡ ከዚህ ይልቅአካፋን ጫፉ ስለትነት ያለው፣ አራት ማዕዘን የሆነ፣ በረዥሙ የእንጨት እጀታው ጫፍ ላይ ብረትየተሰካለት ወይም ደግሞ ጥብቅ የሆነ ፕላስቲክየተገጠመለት እና ከበርካታ ተግባራቱ መካከል የከብቶችን አዛባ ለመፈንጨትወይም ለመበተን የምተቂም መሳርያ በሚል መግለጽ እና ማደናገርይቀናቸዋል፡፡ ብዙዎቹ ቢሮክራቶች የተካኑበት እንደዚህያሉ አቀራረቦችን በማራመድ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

[ጥቂቶች የአጥኝ ቡድኑን የጥናት ግኝት የቢሮክራሲ ዋና መለያ ባህሪ ሆኖ አግኝተውታል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርበው በጥናትቡድኑ የምርመራ ግኝት ላይተመስርቶ ስለቢሮክራሲ የተገለጸ የእራሴ የእንግሊዝኛ (ያማርኛ ትርጉ) ትርጉም ነው፡፡የምርመራ ቡድኑን ግኝት በተመለከተ ከዚህ በላይ እንደተጠቀሰውየሮማውያን ቁጥሮችን እንደዋቢ ማጣቀሻ መውሰድይቻላል፡፡]

[I] በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ አስተዳደር እና በሌሎች አገሮች የሚገኙት የባንኩ ኃላፊዎች የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶችየሚል ፕሮግራም ነድፈውበህዝቦች ላይ ምንም ዓይነት አደጋ አያስከትልም ብለው በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያያሉ የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች ምንም ዓይነት ስራ የማይሰሩለይስሙላ የተቀመጡ ናቸው ፡፡ ፕሮግራሙን በስራ ተርጉመውእንዲያሳዩ በኃላፊነት ቦታ ላይ ብቃት አላሳዩም፡፡

የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች ወይም ደግሞ ኃላፊዎች በጋምቤላ ህዝቦች የመንደር ምሰረታ ፕሮግራም ለውጥ አመጣ አላመጣወይም ደግሞ ፋይዳ ያለው ነገርአስገኘ አላስገኘ ደንታቸው አይደለም፡፡ ከዚህም በላይ ስለይፋ የፖሊሲ እና የመመሪያሰነዶቻቸው ስለጋምቤላ ህዝቦች መሰረታዊ አገልግሎቶች ለማቅረብጥናት ሲጠና በፕሮጀክት ትግበራ ሂደቱ ወቅት በአኟክማህበረሰብ ላይ ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ጉዳቶች እና አደጋዎች የተጠናና እና በሰነዱ ላይ የተካተተምንም ዓይነት ነገር የለም፡፡የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች ወይም ኃላፊዎች ይህን የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮግራም በአራት ክልሎች ላይ በአንድጊዜለመተግበር የመሞከራቸው ሁኔታ ሲታይ ሊውጡት ከሚችሉት በላይ እያኘኩ የሚገኙ መሆናቸውን በግልጽ ያመላክታል፡፡በፕሮጀክት ማጽደቅ ወቅትበባንኩ የፖሊሲ ሰነድ በተራ ቁጥር 2.20 ላይ ከተጠቀሰው ጋር አብሮ የማይሄድ መሆኑእየታወቀ ወደተግባር እንዲገባ መደረጉ የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎችወይም ኃላፊዎች ከሚከተሉት ውስጥ አንደኛውን ሊሆኑእንደሚችሉ ያመላክታል፡ የሙያ ብቃትየለሽነት፣ የለየላቸው የስራ ጸር የሆኑ ሰነፎች፣ ለምንም ነገርየማያስቡ ግዴለሾች፣በቀጣይነት በህዝቦች ላይ ሊመጣ ስለሚችለው ጉዳት እና አደጋ የማያውቁ ክህሎቱ የሌላቸው ደንቆሮዎች፣ ምንም ዓይነትደንታየሌላቸው እና የሞራልም ሆነ የሙያ ስብዕና የሌላቸው ለህዝብ መብት ኬሬዳሽ የሚሉ ከንቱዎች መሆናቸውንያሳያል፡፡ መፍትሄውን ከቦርጫቸው ስርተወሽቆ ያገኙታል!

[II] የዓለም ባንክ ሀገራዊ ፕሮግራም ስራ አስፈጻሚዎች ወይም ኃላፊዎች ምንም ዓይነት ብቃት የሌላቸው እና ኃላፊነትየማይሰማቸው እንዲሁም ደንታቢስ የመሆን እና የሙያ ብቃት የሌላቸው፣ ፕሮጀክቱ በመተግበሩ ምክንያት በአኟክማህበረሰብ ላይ ወደፊት እና አሁንም በትግበራ ወቅት ሊያስከትልየሚችለውን ጉዳት እና አደጋ መለየት የማይችሉ እናየመሰረታዊ አገልግሎት ፕሮጀክቱ ሲተገበር ለህዝቡ ምን ፋይዳ ያለው ነገር እንደሚያመጣ ግንዛቤውየሌላቸው ናቸው፡፡አንድ ጊዜ ጉዳቱ መድረስ ከጀመረ እና የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች ነገሮች በመጥፎ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ካወቁስህተቶቻቸውንመቆጣጠር እና በእነርሱ ስር እንዲሆኑ ለማድረግ አይችሉም፣ ወይም ደግሞ የማስተካከያ እርምጃዎችንመውሰድ አይችሉም ምክንያቱም ወደፊት ምንሊሰሩ እንደሚችሉ የሚያውቁት ነገር የሌላቸው የሙያ ብቃት የለሾችናቸው፡፡ ስለሆነም እነርሱ ባለማወቅ ያደረሱትን ታላቅ ጥፋት ለመፍታት የሚችልሌላ ኃይል የለም ብለው በማሰብእጆቻቸውን አጣጥፈው በመቀመጥ ወይም ደግሞ የስራ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ባለመቻል በአቅመቢስነትመሳቂያ፣ሰነፍ፣ የደከመ አቅመቢስ እና ተነሳሽነት የሌለው ሆነው በወራዳ ተግባራት ተፈርጅው ከመቀመጥ ምንም የጨመሩት ነገርየለም፡፡

[III] ፕሮጀክቱን ከማቀድ ጅምሮ እስከ ትግበራው ወቅት ጊዜ ድረስ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች አቅመ ቢሶች ነበሩወይም ደግሞ የባንኩን የፖሊሰሰነድ ተራ ቁጥር 4.10 [መመሪያዎች እና ፖሊሲዎች የባንኩ ፕሮግራም የሰዎችን ክብር ሙሉበሙሉ እንዲያከብር፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ፣የኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ነገሮች ሁሉእንዲያከብሩ የሚያረጋግጥ] የሚያስገድደውን ሰነድ ሆን ብለው የማያውቁ ደንቆሮዎች ናቸው፡፡ሆኖም እስከ አሁንም ድረስበአኟክ ማህበረሰብ ላይ የደረሰውን ጉዳት ከግንዛቤ በማስገባት ተመጣጣኝ የሆነ የመፍትሄ እርምጃ በመውሰድሁኔታውንእንደገና የማሻሻል እና ጉዳቱን የመቀነስ ስራ መስራት ይቻል ነበር፡፡ ይህንንም ለማድረግ የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች ተጠቃሚይሆናል የተባለውንህዝብ በመሰብሰብ በጋራ ከህዝቡ ጋር መመካከር እና ወደፊት በዚህ ፕሮግራም ጉዳት ሊደርስባቸውይችላል ከሚባሉ ህዝቦች ጋር በመመካከር ባህሉንበማያዛባ መልኩ ጥቅሞቻቸውን ሊያስከብር የሚችል የመፍትሄ እርምጃመውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ቋሚ ህዝቦችን ለዘመናት ከኖሩበትቀያቸው በማፈናቀል ከኖሩበት የተሻለ ጥቅምበሌለበት ሁኔታ ማንገላታት ተገቢ አይደለም፡፡

[IV] በኢትዮጵያ ያሉ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች ቆሎ አየቆረጠሙ መራመድ የማይችሉ ፍጡራን ናቸው፡፡ ቀኝ እጃቸውየግራ እጃቸው ምን እየሰራእንደሆነ የሚያውቁ ናቸው ፡፡ የዓለም ባንክ የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት የኢኮኖሚያዊተጠቃሚነት ያላገኙትን ማህበረሰቦች የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነትባለው መልኩ በማህበራዊ እና በመሰረተ ልማት ዝርጋታእንዲሁም የመሰረታዊ ትምህርት፣ የጤና፣ ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽ እንዲሆኑ እናየህብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታእንዲሻሻል ማድረግ ማስቻል ነው፡፡ የጋምቤላ ህዝብ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3 የአቅም ግንባታ ስራእንዲጠናከር፣ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና ትክክለኛ የሆነ የገንዘብ አስተዳደር በየክልሎቹ እንዲኖር እና መሰረታዊአገልግሎቶች ማለትም እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣የውኃ አቅርቦት እና ንጽህና እንዲሁም የገጠር መንገዶች ተሟልተውእንዲቀርቡ ለማድረግ ነው፡፡

የባንኩ የስራ አስፈጻሚዎች በምቹ ወንበሮቻቸው ላይ ተንፈላስሰው በመቀመጥ ክትትል የማድረግ እና ሁለቱንምፕሮግራሞች የማስተባበር ስራቸውንአልሰሩም፡፡ በዚህም መሰረት የአኟክ ማህበረሰብ ቅሬታውን እንዳቀረበው ሁሉየጋምቤላ ህዝብ ከጉዳት እና ከአደጋ ላይ ተጥሎ ይገኛል፡፡ በሌላ አገላለጽየባንኩ የስራ አስፈጻሚዎች ስራቸውን በአግባቡባለመስራታቸው ምክንያት የአኟክ ማህበረሰብ ለምነቱ ወደተሟጠጠ ጠፍ መሬት ላይ ተወስዶ እንዲሰፍርተደርጓል፣እንዲሁም ትምህርት ቤቶች፣ ክሊኒኮች፣ የውኃ ጉድጓዶች ወይም ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች የሌሉበት አዲስ መንደርበግዳጅ እንዲመሰርትተደርጓል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ጥቂት የአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የአኟክ ማህበረሰብ አባላት እናልጆቻቸው በመንደር ምስረታ ፕሮግራሙ ምክንያት በረኃብህይወታቸው አልፏል፡፡ ሌሎቹ የግዳጅ የሰፈራ ፕሮግራሙንየተቃወሙትን የአኟክ ማህበረሰብ አባላት በቁጥጥር ስር በማዋል፣ የድብደባ፣ የስቃይ እናየግድያ ሰለባ ዒላማ እንዲሆኑተዳርገዋል፡፡ ይህ ድርጊት የጋምቤላ እና የዓለም ባንክ ከመሆኑ በስተቀር ጥንታዊ የሮማ ከተማ የሆነችውን የፖምፔየእሳትቃጠሎ እና እርባናየለሽ ድርጊትን ከመፈጸም የሚለየው ነገር የለም፡፡

በኢትዮጵያ ባሉ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጸሚዎች እጆች ላይ ደም አለ!

[V] በኢትዮጵያ በአኟክ ህዝብ ላይ የዓለም ባንክ ያደረሰውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ለመደበቅ ሲባል ዓለም ባንክ እራሱጥፋተኝነቱ እንዳይተወቅ የዝምታሽረባ ዱለታ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የጋራ ጉባኤ ተልዕኮ ዋና ዓላማው በፕሮጀክቱ ሁሉምአካሎች ላይ የሚታየውን መሻሻል ለመገምገም እና የትግበራድጋፍ ለማድረግ ነው፡፡ የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ መስከረም 2012ለህዝቡ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3 ማስፈጸሚያ የሚውል 600 ሚሊዮን ዶላርሰጥቷል፡፡ የመሰረታዊአገልግሎቶች ፕሮጀክት 3 መተግበር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የዓለም ባንክ ሶስት የጋራ ግምገማዎች ያደረገ ሲሆን በአኟክህዝቦች ላይስለደረሰው ጉዳት አንዳችም ቃል ትንፍሽ ሳይል አልፎታል፡፡ የዓለም ባንክ “የኢንቨስትመንት የማበደር ፖሊሲ(OP/BP 10.00)” ስለፖሊሲው፣ ስለአካሄድስርዓቱ፣ ስለፕሮጀክቱ አፈጻጸም እና ክትትል በተበዳሪው ወይም በፕሮጀክቱተጠቃሚዎች፣ ስለፕሮጀክቱ አፈጻጸም እና ስለስምምነቱ የተፈጻሚነት ደረጃዝርዝር የሆነ የፖሊሲውን መግለጫ ይሰጣል፡፡የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች በስራዎቻቸው ላይ ለጥ ብለው ተኝተዋል ወይም ደግሞ አውቀው ሆንብለው ስለባንኩየኢንቨስትመንት እና ክትትል ፖሊሲ ምንም አናውቅም በማለት አድፍጠዋል፡፡

[VI] በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች የባንኩ ገንዘብ በወረዳ ደረጃ ቁጥጥር ይደረግበታል ሲሉ ግልጽ የሆነውሸትን ዋሽተዋል እንዲሁም ታላቅየልብ ወለድ ትረካን ተርከዋል፡፡ የዓለም ባንክ ሰነድ በተራ ቁጥር OMS 2.20 ላይየተቀመጠው ባንኩ ከሁሉም ነገር በላይ ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ተግባራትከተበዳሪው ዓለም አቀፍ ስምምነት አንጻርአካባቢን፣ ጤናን፣ እና አጠቃላይ የህዝቦችን ደህንነት በሚያረጋግጥ መልኩ መታየት እንዳለባቸው ያስገነዝባል፡፡OP/BP 10.02 የሰነዱ ክፍል እንደሚያመላክተው በፕሮጀክት ትግበራ ወቅት ባንኩ የገንዘብ አጠቃቀሙን እና አያያዝ ሁኔታእንዲሁም ያለው ገንዘብ በቂመሆን አለመሆኑን መከታተል እና መገምገም እንዳለበት በግልጽ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ የባንኩ ስራ አስፈጻሚዎች አቅመቢሶች ወይም ደግሞ ሆን ብለው ታላቅ ኃላፊነትን ይዘው ኃላፊነታቸውንግን በአግባቡ ለመወጣት ግንግድ የሌላቸው ደንታቢሶች ናቸው፡፡ ወረዳዎች ከክልሎች እና ከዞኖች በመቀጠል በሀገሪቱያልተማከለ አስተዳደራዊ ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ በሶስተኛነትደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ ወረዳዎች በጣም ጉልህ የሆነ የሙስናወንጀል የሚፈጸምባቸው ማዕከላት ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫለህወሀት 99.6 በመቶ የድምጽውጤት እንዲገኝ ያደረጉት የወረዳ ምክር ቤቶች ናቸው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በኢትዮጵያ ያሉ የዓለም ባንክ ስራአስፈጻሚዎችየራሳቸው የሆነውን ስራ እና ሙያዊ ተግባራቸውን እርግፍ አድርገው ትተው በጭፍንነት ታማኝነት ለሌላቸው እና ስለገንዘብአያያዝ እናአስተዳደር ምንም ዓነት እውቀት ለሌላቸው ለወረዳ ሙሰኛ ባለስልጣኖች ሰጥተው በህዝብ ስም ለህዝብ የመጣንየብድር ገንዘብ እንዲባክን በማድረግ ላይይገኛሉ፡፡ (ምንድን ነበር የሚያስቡት? ያንን ጣያቄ እንዲጫር አድርግ!)

[VII] [ይህ ግኝት የገንዘብ ተጠያቂነት ጉዳይ እስከተነሳ ድረስ እጅግ በጣም የሚያስገርምና የሚያስደንቅ ነው፡፡] በኢትዮጵያያሉ የዓለም ባንክ ስራአስፈጻሚዎች የባንኩን ገንዘብ ከሙስና ለመከላከል የሰሩት አንዳችም ነገር የለም፡፡ ለዚህም ነው“በመጀመሪያ ብቁ ያልሆነ የፋይናንስ አደጋ“ የሚል ሀረግየተጨመረው፡፡ የዓለም ባንክ OP/BP 10.00 እና የትንተና መሳሪያዎች (የህዝብ ወጭ እና የገንዘብ ተጠያቂነት) (ህወገተ) በተቀባይ ክልሎች የሚላከውገንዘብ እንዳይባክንየተዘጋጀው፡፡ እነዚህ ፖሊሲዎች እና የትንተና መሳሪያዎች አጠቃላይ በሆነ መልኩ የሙስናን አደጋ ይከላከላሉ ባይባልምአጠቃላይበሆነ መለኩ ግን ዕቅድ፣ ክትትል እና ግምገማዎች የሚካሄዱ ከሆነ በተቀባይ አገሮች ላይ አዎንታዊ የሆነ ውጤትንያመጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ የዓለምባንክ ስራ አስፈጻሚዎች ስለገንዘብ አደጋ የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ፕሮጀክት 3ንእንዳለ ለሙሰኞች እና ለዘራፊዎች ትተውታል!

ስለዓለም ባንክ የአሰራር ሁኔታ እና ቅዱስ ስላልሆነው ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች የልማት አጋርነት ቡድንእየተባለ ለሚጠራው መንግስታዊያልሆነ አካል አዲስ አይደለሁም፡፡ የእነዚህን አካላት ዘገባዎች አጥንቻለሁ፣ እናምፖሊሲዎቻቸውን፣ የትግበራ ሰነዶቻቸውን፣ መመሪያዎችን እና ለህዝብየሚሰጡ መግለጫዎችን እንዲሁም ሌሎችንህትመቶች እስካሁን ድረስ አጥንቻለሁ፡፡ ከዚህ አንጻር ስለፖሊሲዎቻቸው፣ ተሞክሯቸው እና በኢትዮጵያእያከናወኗቸውስላሉት ተግባራት ግንዛቤ አለኝ ብዬ መናገር እችላለሁ፡፡

“በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ የተለቀቀውን ባለ 417 ገጽ የዓለም ባንክን ዘገባ ከጸሀፊዎቹበስተቀር ምናልባትም ከማንምበበለጠ ሁኔታ ለበርካታ ጊዜ ደግሜ እና ደጋግሜ ያነበብኩት እኔ እሆናለሁ የሚል ግምትአለኝ፡፡ በእርግጥ ያንን ዘገባ ለበርካታ ጊዜ አንብቤዋለሁ፣ እናምምን ያህል ጊዜ እንደሆነ ለህዝብ ለመናገር ሀፍረትይሰማኛል፡፡ ያንን ዘገባ በመጠቀም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና የህወሀትን የሙስና ግዛት ለማጋለጥ በርካታበሙስና ላይያነጣጠሩ ተችቶችን በማዘጋጅበት ጊዜ ተጠቅሜበታለሁ፡፡

የሙስና ዘገባ ማዘጋጀት ንጹህ አየር የመተንፈስ ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እቀበላለሁ፡፡ የዓለም ባንክ የሙስና ዘገባ እንደዚህእንደ ኢትዮጵያ ያለ ጥልቀት፣ወርድ እና ስፋት ያለው በሌሎች ሀገሮች ላይ እስከ አሁን ድረስ አላየሁም፡፡ አንድ ነገር ህልውከሆነ ለማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያያለውን የሙስናን ጥልቀት እና ስፋት ጥልቀት ባለው ሁኔታ አጥንቶበማቅረቡ እና የህወሀት የሙስና የግዛት አድማስ በመጋለጡ የተሰማኝ ደስታ ወደርየለውም፣ ከዚህም በላይ ይህንን ጥናትያቀረበውን እና እውነታውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ያደረገውን ዓለም ባንክን ከልብ አመስግኘ ነበር፡፡“በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ የሚለው የዓለም ባንክ የጥናት ዘገባ የግልጽነት እና የተጠያቂነትን ጉዳይ አስመልክቶ አዲስምዕራፍ ለመክፈትእንደቻለ እምነት አለኝ፡፡ በኢትዮጵያ ወይም በሌሎች ሀገሮች ያሉትን የባንኩን ፕሮግራሞችንየሚያስፈጽሙትን ሁሉንም የዓለም ባንክ ሰራተኞች የመክሰስዓላማ የለኝም፡፡ ጥቂት የሆኑ መልካም ስብዕናን የተላበሱ እናስለኢትዮጵያ እውነቱን ብቻ የሚናገሩ እና በመሸበት ማደር የሚፈልጉ እውነተኛ እና ሀቀኛየዓለም ባንክ ሙያተኞች አሉ፡፡ከእነዚህም መካከል በዓለም ባንክ ውስጥ የሚገኙ ወልፍጋንግ ፌንግለር የተባሉት ታዋቂ የኢኮኖሚ ጠበብትአንዱናቸው፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ረኃብ እና የምግብ እህል እጥረት የለም በማለት ለመካድሙከራ አድርጎ ነበር፡፡ ፌንግለርግን ሽንጣቸውን ገትረው ፊትለፊት ተከራከሩት፡፡ ፌንግለር እንዲህ አሉ፣ “በአፍሪካ ቀንድያለው የረኃብ ቀውስ ሰው ሰራሽ ነው፡፡ ድርቆች በተደጋጋሚይከሰታሉ፣ ሆኖም ግን ያንን ድርቅ ለማስወገድ በሚል ሌላመጥፎ የሆነ እና ሌላ ድርቅ እና ረኃብን ሊያመጣ የሚችል ፖሊሲ ትነድፋላችሁ፡፡ በሌላአባባል በኢትዮጵያ ለረሀብበተደጋጋሚ መከሰት ትልቁ ችግር ድርቁ ሳይሆን የመልካም አስተዳደር እጦት ነው::”

ሁልጊዜ ስለሚከሰተው ረኃብ ዓለም አቀፍ የእርዳታ እና የብዙህን አገሮች አንድ ዓይነት የቢሮክራሲያዊ ቋንቋን በመፍጠርለማደናገሪያነት በመጠቀም ረሀብየሚከሰተው በመልካም አስተዳደር እጦት እና ትክክለኛ ፖሊሲ ቀርጾ መንቀሳቀስ ሳይቻልበመቅረቱ የሚለውን ቸል በማለት ሌሎችን ፍሬከርስኪ ነገሮችንእያመጡ ህዝብን በማደናገር ላይ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳሬክተር የሆኑት እንደ ጓንግ ዠ ቸን ረዥም ለብ ወለድ ትርኮችን መናገር የሚችሉ ሰዎች አሉ፡፡እ.ኤ.አ ታህሳስ 2012 ቸን እንዲህብለው ነበር፣ “በኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት በመፈጠሩ ምክንያት የድህነትደረጃውን እ.ኤ.አ በ2004/05 እና 2010/11 ባሉት ዓመታት መካከልቀደም ከነበረበት ከ38.7 በመቶ ወደ 29.6 በመቶበማውረድ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለት ሚሊዮን ተኩል የሚሆኑ ዜጎች ከድህነት ተላቅቀዋል…መንግስት እ.ኤ.አበ2014/15 ድህነትን ወደ 22.2 በመቶ ለማድረስ የያዘው ዕቀድ በጣም የተጋነነ ይመስላል፣ ሆኖም ግን ሊደረስበት የሚችልነው፡፡“

እንደ አቡጀዴ ከመቀደድ በላይ የሚያሳፍር ምን ነገር ሊኖር ይችላል ወገኖቼ?!

በአሁኑ ጊዜ ያለንበት ዓመት 2015 ነው! ስለዚህ በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ድህነት በ22.2 በመቶ ወርዶ ይታያልን!? አቤትቅጥፈት! ወይ አይን ማውጣት!

ይገባኛል! በርግጥ ጉዳዩ ይገባኛል፡፡ የዓለም ባንክ ሰዎች ህወሀት እራሳቸውን ጥሩ አድርጎ እንዲስላቸው እነርሱ ደግሞህወሀትን ጥሩ ስዕል እንዳለውአድርገው ያቀርባሉ፡፡ የዓለም ባንክ ሰዎች ለህወሀት ትክክለኛውን ነገር ከተናገሩ ለእነርሱለእራሳቸውም ትክክለኛውን ነገር ይናገራሉ ማለት ነው፡፡ እነርሱስለህወሀት ስህተት ተናጋሪ ሆነው መቅረቡን አይፈልጉምምክንያቱም እነርሱም የሚያደርጉትን ያውቃሉና፡፡ በዚህም መሰረት ህወሀትን ለመጠበቅ ሲሉህዝብ በረሀብ እያለቀ እናበድርቅ ሲጎዳ በዓይናቸው እየተመለከቱ ለዝምታ ጸጥታው ዱለታ ተባባሪ ሆነው ህሊናቸውን ሸጠው ይታያሉ፡፡

የህወሀት ሙስና፣ ኢኮኖሚውን ማስተዳደር ያለመቻል እና በጋምቤላ ክልል በሰው ልጆች ላይ እየፈጸሙ ያሉት የመብትድፍጠጣ ተንሰራፍቶ እየታየየዓለም ባንክ ሰዎች ዓይናቸውን ጨፍነው፣ ጆሯቸውን ደፍነው ሆኖም ግን አፋቸውን ከፍተውየቅጥፈት አፈታሪክ በማውራት በኢትዮጵያ ልብወለድ የሆነየኢኮኖሚ ዕድገት እንዳለ አድርገው ይነግሩናል፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2012 የዓለም ባንክ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከአፍሪካ አህጉር የኢኮኖሚዕድገት ሁለት ጊዜ እጥፍ በሚሆንመልኩ እ.ኤ.አ ከ2004 ጀምሮ በየዓመቱ በአማካይ በ10.6 በመቶ የሀገር ውስጥ እድገትእያስመዘገበ የመጣ ሲሆን ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገሮች 5.2 በመቶዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ሲነጻጸር እጅግ ትልቅመሆኑን አንድ የዓለም ባንክ አዲስ ዘገባ ይፋ አድርጓል፡፡“

በእርግጥ የዓለም ባንክ የወያኔ ሸፍጥ እንደሆነ ያውቃል…! ከምንም ጥርጣሬ በላይ በሆነ መልኩ እንደሮኬት እየተተኮሰየሚነገረን የቅጥፈት የኢኮኖሚዕድገት መጣኔ እና ሌሎችም ተመሳሳይ የሆኑ በህዝብ ላይ የሚደረጉ የቅጥፈት አሀዞች ሁሉበመለስ ዜናዊ የቁጥር መመቀያ የስታቲስቲክስ ቢሮ እየተመረቱእየወጡ ለዓለም ባንክ፣ ለዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እናለሌሎችም እንደ ሀገራዊ እና የውጭ ድርጅቶች እንደ በቀቀን እንዲደግሙት በጸጥታ እየወጡየሚሰጡ እና በመጨረሻምመለስ ሁለተኛ ዘገባ አቅራቢ ሆኖ ባዶ የተፈበረከ ቁጥር እየጠራ እድገት ነው እያለ ከረባቱን እና መነጽሩን እያሳመረሲያሰለችንኖሮ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ሲሰናበት አሁን ድግሞ የቅጥፈት ጓዶቹ የሆኑትን ደቀመዝሙሮቹን ተክቶልንአልፏል፡፡ “የመለስ ዜናዊ የቅጥፈት ኢኮኖሚክስ“በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችቴ ላይ ያቀረብኩትን ትንተና ከዓለምባንክ ወይም ደግሞ ከሌላ በመምጣት ማንም ሙያው እና እውነታው አለኝየሚል ቀርቦ ማስተባበል እንዲችል የመሞገቻመድረክ ለመክፈት ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ ሙግቴንም ማንም ተቀበሎ ሊሞግተኝ አልቻለም። ሆኖም ዉቸትአንዴት ዉነትንልሞግት ይችላል?

የሞተ እርዳታ/Dead Aid መጽሐፍ ደራሲ የሆነችው ዳምቢሳ ሞዮ በመጽሐፏ ላይ እንዲህ የሚል ጹሁፍ አስነብባለች፣ “…የዓለም ባንክ የጥናት ግኝትእንደሚያመለክተው 85 በመቶ የሚሆነው የልማት ዕርዳታ ከታቀደለት ዓላማ ውጭ ነውየሚውለው፡፡ ለጋሽ ሀገሮች በጣም ሙሰኛ የሆኑ አገዛዞችንእየፈለፈሉ ነው፡፡ እ.ኤ.አ ከ1980 እስከ 1996 ባሉት ዓመታትውስጥ ብቻ የዓለም ባንክ 72 በመቶ የሆነው ዕርዳታ ለህጉ ለማይገዙ ሀገሮች የተሰጠ ነው፡፡የለጋሽ ሀገሮችን መለገስእንዲችሉ የሚቀርበው ዕርዳታ የመፈለግ ጥያቄ በምንም ዓይነት ሁኔታ እርካታን የሚያገኝበት ሆኖ አልተገኘም፡፡“

እ.ኤ.አ ህዳር 2014 በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ዘገባ የሞዮን አባባል የሚደግፍ ንጹህ እና አወዛጋቢ ያልሆነማስረጃ አቅርቧል፡፡ ባለፉትሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ ምን ያህል ትንሽ ነገሮች ተለውጠዋል?!

የዓለም ባንክ አስመሳይነት በኢትዮጵያ፣

የዓለም ባንክ ተልዕኮ “በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ትውልድ የእድሜ ጣሪያ ስር አስከፊ የሆነውን ድህነትን ማጥፋት“ እና“የጋራ ብልጽግናን“ ማራመድየሚል ነው፡፡ ባንኩ ይህንን ዓላማ ለማሳካት በሚል በኢትዮጵያ ይህንን ተልዕኮ ለማሳካት ሲልየኢትዮጵያ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥበቃ የሚልፕሮጀክት (መአጥፕ) ነድፎ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ እንደ የዓለም ባንክዘገባ ከሆነ መአጥፕ በኢትዮጵያ ውስጥ አራት ክፍሎች አሉት፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) በክልል እና በአካባቢ መንግስታት የሚሰጡ መሰረታዊ አገልግቶችን የማከፋፈል ስራ መስራት እና መከታተል፣

2ኛ) ለመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አገልግሎት ንዑስ ፕሮግራሞች በጣም አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ለማቅረብየሚያስችል አስተማማኝ የሆነ የገንዘብእገዛ ማድረግ፣

3ኛ) በክልል፣ እና በከተማ አሰተዳደሮች፣ በወረዳ እና በንዑስ ወረዳ ደረጃ አጥጋቢ በሆነ መልኩ ግልጽነት እና የህዝብ በጀትአጠቃቀም ስርዓትን መጠበቅእንዲሁም በበጀት ዝግጅት እና በአገልግሎት አቅርቦት ጊዜ ዜጎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉማበረታታት እና ውክልናም እንዲኖራቸው ማድረግ፣ እና

4ኛ) የዜጎችን ድምጽ ለማጠናከር እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በመውሰድ እንዲሁም ዜጎች በበጀት ዝግጅት ሂደትላይ በንቃት መሳተፍ እንዲችሉየተመረጡ አካሄዶችን በመውሰድ የናሙና ሙከራ የአቅም ግንባታ ስራዎችን መስራት፡፡

የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ በኢትዮጵያ ለመአጥፕ ፕሮግራም እገዛ በማድረግ የ2 ቢሊዮን ዶላር ቃል ገብቶ እገዛበማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉትሁለት ዓመታት ብቻ ባንኩ ከፍተኛ የሆነ ማለትም 600 ሚሊዮን ዶላር ወጭ አድርጓል፡፡

እውነታው ግን የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች ተልዕኮ በአሳዛኝ ሁኔታ ከሽፏል፡፡ በአራቱ ክልሎች የሚካሄደውን የመአጥፕየመንደር ምስረታ ፕሮጅከት 3ዝርዝር የጉዳት ትንተና ሳይካሄድ በመቅረቱ ውድቀትን ተከናንበዋል፡፡ የባንኩን የድርጊትመርሀ ግብር እና መመሪያዎችን ሳይከተል የሚሰራ ስለሆነ ከባንኩእምነት ውጭ ተጻራሪ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ስለሆነዓላማውን ስቷል፡፡ ባንኩ ፕሮግራሙን በሚተገብርበት ጊዜ ከአኟክ ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦመወያየት እና መመካከርስላልቻለ በህዝቦች ላይ የሚመጣው አሉታዊ ተጽዕኖ በመኖሩ ፕሮግራሙ ውድቀት ደርሶበታል፡፡ ስመአጥፕ ፕሮጀክት 3እናስለማህበረሰቡ የልማት ፕሮግራም ስለጉዳት ትንተና በሰነዱ ማዕቀፍ ላያ በተያዘው መሰረት ስላልተሰራ አቅመቢስመሆናቸውን በግልጽ አመላክቷል፡፡የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች ከአኟክ ማህበረሰብ ጋር ቀጥታ ግንኙነት እና ጥብቅትስስር ካለው ከመሬት እና ከሌሎች ሀብቶች ከማግኘት አንጻርስለህዝቡ የኑሩ መሻሻል ሁኔታ፣ ስለህዝቡ ደህንነት እናስለመሰረታዊ አገልግሎቶች ተደራሽነት ደንታ የላቸውም፡፡

በጋራ ግምገማቸው እና ፕሮጀክቱን በመተግበር ጊዜ ስለሚሰጡት እገዛ ዘገባዎች የይስሙላ እየቀባቡ የተሳሳቱ መረጃዎችንበመስጠት ወይም አስፈላጊያልሆኑ እውነታዎች ናቸው ብለው የሚያምኑባቸውን በማጥፋት ግልጽነትን እና ተጠያቂነትንእንዲጠፋ አድርገዋል፡፡ ብዙ የዕቅድ ስራዎችን፣ የክትትልወይም የቁጥጥር ስራዎችን ባንኩ እየሰራ አይደለም፡፡ ሙያዊ የሆነስራቸውን እና ግዴታዎቻቸውን እርግፍ አድርገው በመተው በመቶ ሚሊዮኖችየሚቆጠር ዶላር የሚካሄድ ፕሮግራምማስፈጸሚያን ገንዘብ በሙስና እስከ አንገታቸው ድረስ ለተዘፈቁ የወረዳ ኃላፊዎች አስረክበዋል፡፡ እኔ ይኸ ጉዳይበጣምያሳስበኛል፣ ለምን እንደሆነ ለማወቅም ጉጉት ያድርብኛል፡፡ለመሆኑ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጸሚዎች በየዕለቱ ምን ሲሰሩ ነውየሚውሉት? (ነገስታታ ቀኑን ሙሉ ምን ይሰራልይ ብሎ መጠየቁ ይቀላል።)

ድምጼን ከፍ አድርጌ በመጮህ ምን ዓይነት ግራ የሚያጋባ መርሀግብር ነው የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በመተግበር ላይያለው?

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2013 የዓለም ባንክ ቡድን ፕሬዚዳንት የሆኑት ጅምዮንግ ኪም እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር፣“በመልማት ላይ ባሉ ሀገሮች ሙስናየህዝቦች ቁጥር አንድ ጠላት ነው… ሙስናን በምንም ዓይነት መንገድ ልንታገሰውአንችልም፣ እናም ባለን ስልጣን እና ኃይል ተጠቅመን ይህንን እኩይድርጊት ለማጥፋት ከእርሱ ጋር በጽናት መታገል አለብን…እያንዳንዷ ዶላር በሙስና የተዘፈቀ ባለስልጣን ወይም ደግሞ የቢዝነስ ሰው ወስዶ ከኪሱየሚጨምራት ጤናዋን ለመጠበቅከተሰለፈችው ነፍሰጡር ሴት ወይም ደግሞ ትምህርትን ከምትፈልግ ልጃገረድ ወይም ልጅ፣ ወይም ውኃ፣ መንገድ፣እናትምህርት ቤቶችን ከሚፈልጉ ማህበረሰቦች ሰርቆ የሚውስዳት ናት፡፡ ከዓለምነው ግብ ለመድረስ እና አስከፊ የሆነውንድህነት እ.ኤ.አ በ2030 ከዓለምለማጥፋት እና የጋራ ብልጽግና ለማራመድ እያንዳንዷ ዶላር የወሳኝነት ሚናትጫወታለች፡፡“

ኪም እ.ኤ.አ በ2015 ወደ ጋምቤላ መጥተው ወንድሞቼንና እህቶቼን ቢጎበኙ እና የእርሳቸው ባንክ ስንት ትምህርት ቤቶች፣ሆስፒታሎች፣ ኪሊኒኮች፣መንገድች እና የውኃ ግድጓዶች በ600 ሚሊዮን ዶላር እንደሰራላቸው ለወገኖቸ እንዲነግሯቸውምኞቴ ነው፡፡

ድምጼን ከፍ አድርጌ በመጮህ: አዲስ አበባ ያለውን የዓለም ባንክ ሰራተኞች ቀኑን ሙሉ ሲያዛጉ ነው የሚዉሉት?!

(ይቀጥላል…)

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

http://satenaw.com/amharic/archives/4197#

The Committee to Protect Journalists (CPJ), Oakland Institute (OI) and Survival International (SI) have strongly rejected and condemned Dawit Kebede’s recent allegations

CPJ, rights groups slam Dawit Kebede over allegations

January 27, 2015

NED cancelled Awramba Times funding over concerns

by Tamru Ayele

The Committee to Protect Journalists (CPJ), Oakland Institute (OI) and Survival International (SI) have strongly rejected and condemned Dawit Kebede’s recent allegations against several global advocacy groups.  The groups said such an irresponsible and unsubstantiated allegation that has no factual basis is not expected of someone who claims to a journalist committed to informing others.Dawit Kebede’s recent allegations against CPJ

Dawit Kebede, who was one of the four recipients of CPJ’s International Press Freedom Award in 2010, recently appeared on the state-run ETV and accused CPJ, Oakland Institute , Freedom House, Human Rights Watch, Amnesty International, International Rivers, Survival International and the International Crisis Group of being tools of imposing Western hegemony. “These organizations are part of an overall allegiance to control the world under one single ideology,” he had asserted.

Sue Valentine, CPJ Africa Program Coordinator,said in a statement that CPJ was very disappointed with Kebede’s unwarranted attacks. “We were hurt and disappointed when we read articles summarizing a television interview with Dawit in which he was critical of CPJ.”

Sue Valentine, CPJ Africa Program Coordinator

Valentine indicated that CPJ had requested Kebede to clarify his allegations, but blamed it on inaccurate translation. CPJ had the 28-minute long interview translated and verified that the former press freedom hero had indeed tried to defame the reputable defender of press freedom with allegations that are contrary to the missions of the organization. CPJ also campaigned for the release of Kebede when he was unjustly incarcerated in 2005.

“CPJ honored Dawit Kebede based on his journalistic work prior to 2010,” Valentine noted. “Based on his recent TV interview, he appeared to have changed his views. We do not know why, but he is obviously entitled to his opinion. However, CPJ strongly rejects any suggestion that we seek to impose a ‘Western hegemony’ on other countries and continents. CPJ’s sole mandate is to defend the right of all journalist to express their views and to report the news freely,” she added.

According to Valentine, CPJ’s Africa Program defends the right of all journalists working on the continent to report news and opinion freely and independently, without pressure from governments, big business or any other interest groups.

Anuradha Mittal, Executive Director of the Oakland Institute, said on her part that making unsubstantiated allegations without substantiating them with facts is not expected of a journalist. “My advice, despite all obstacles and human rights abuses in a repressive regime, stay true to your profession of journalism.  Like the Oakland Institute, whose mission is to increase public participation and promote fair debate on critical social, economic and environmental issues, do not take things for granted. Research objectively and independently, questioning the official discourse of both governments and NGOs, but seek the truth for yourself,” she advised.

Anuradha Mittal, Executive Director of the Oakland Institute

“If we were controlled by Western governments, our work would not have exposed and challenged the support of the USAID and Dfid of Ethiopia’s “development” strategy and ignoring of human rights abuse. Our work and methodology speaks for itself and we cannot take seriously every allegation made by a journalist who has now made up with a regime that abuses its own citizens. Let us not forget that according to the CPJ 17 journalists are still languishing in the jails while hundreds fled and now live in exile,” she added.

Mittal pointed out that unlike Kedebe’s allegations, all of OI’s reports clearly mention the methodology used and evidence provided to substantiate the allegations of human rights abuses, forced displacement that are being carried out in Ethiopia. “This work has been carried out through extensive field work in the communities impacted, often at great risk to the researchers.  We have also provided documentation such as the recordings and transcripts from investigations carried out by the donors. So this is not about our word against Mr. Kedebe’s words. This is about who has the proof,” Mittal said.

With regard to accusations that organisations like OI are attempting to impede development in Ethiopia, she said that forced displacement of communities from their lands and livelihoods cannot be justified as development. “Ethiopia’s food security is based on food aid and other development aid while it gives away its resources to foreign investors. You don’t need a rocket scientist that this is not development, but a destructive policy in action that will make the country dependent on foreign aid, destroy local communities and their livelihoods and food security, and usher in insecurity and conflicts,” the OI chief noted.

Alice Bayer, Press Officer at Survival International, explained that Survival is an international organization with supporters in about 80 countries around the world, including Ethiopia and China, and defends the rights of  tribal peoples that have developed ways of life that are largely self-sufficient and extraordinary diverse. “Our only goal is for these ways of life to be respected. Of course, this means that we stand for many different ideologies, and tribal peoples’ right to live by them. The Ethiopian government  stands guilty of imposing its aggressive ideology, on the tribes of the Omo Valley, who merely wish to be allowed to live their lives as they choose and not have ‘development’ projects violently forced upon them,” she said.

Funded by their supporters and independent funding sources, the advocacy groups never accept any funding from government agencies.

Meanwhile, the National Endowment for Democracy, which supports democratic institutions around the world, has disclosed that it discontinued funding Awramba Times due to concerns after supporting it between 2011 to 2014.

Jane Jacobsen, NED’s Senior Director, Public Affairs said that the Endowment funded Awramba Times to produce and disseminate content that promotes good governance, transparency, rule of law, human rights and the importance of democratic institutions. “In light of concerns that Awramba Times was not meeting the above project objectives NED discontinued its funding in January 2014.”

According to its annual report, NED’s funding beneficiaries in Ethiopia include Center for International Private Enterprise ($527,008), Debebe and Temesgen Law Office ($72,000), Forum for Social Studies, Peace and Development Center (?) , and Vision Ethiopian Congress for Democracy ($34,992).

The TPLF-led regime has repeatedly accused NED of funding groups and individuals bent on overthrowing the government. Ironically, Mimi Sebhatu, a vocal defender of tyranny in Ethiopia, was one of the recipients of NED’s money. In 2011 Kebede had fled Ethiopia and told CPJ that he had been targeted by pro-government media outlets and Mimi Sebhat, whom he accused of attacking him on her station, Zami FM Radio.

A few years ago, Mimi Sebhatu received $26,740 from NED while Kebede received $36,000 annually from 2011-2014, according to public records. In an ironic twist, both Mimi and Dawit are now attacking individuals and organizations, including CPJ and NED, that expose gross human rights violations in Ethiopia. They are currently funded by  the TPLF-led tyrannical regime, reliable sources say.

http://ecadforum.com/2015/01/27/cpj-rights-groups-slam-dawit-kebede-over-allegations/?utm_source=feedburner&utm_medium=twitter&utm_campaign=Feed%3A%20ecadforum%2FHvBQ%20%28ECADF%20Ethiopian%20News%29

Post Navigation